top of page

ጥር 12፣ 2015- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከሃፊነታቸው በተነሱት ሚኒስትሮች ምትክ አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾሙ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ከሃፊነታቸው በተነሱት ሚኒስትሮች ምትክ አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾሙ፡፡


በዚሁ መሰረትም የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር በነበሩት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ምትክ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር አለሙ ስሜ ተሹመዋል፡፡


የማዕድን ሚኒስትር በነበሩት አቶ ታከለ ኡማ ምትክ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ተመድበዋል፡፡


የግብርና ሚኒስትር በነበሩት እና በቅርቡ በአምባሳደርነት በተመደቡት አቶ ኡመር ሆሴን ምትክ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ሃበት ክላስተር አስተባበሪ የነበሩት ዶ/ር ግርማ አመንቴ ተሹመዋል።


አቶ ታከለ ኡማ፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ አቶ ኡመር ሁሴንና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ በሳለፍነው ቅዳሜ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡


የአዳዲሶቹ የሚኒስተሮቹ ሹመት በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መጽደቅ ይጠበቅበታል።


ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ ከዚህ በተጨማሪም ከጥር 10፣ 2015 ጀምሮ 5 ሹመቶች ሰጥተዋል።


የብሔራዊ ባንክ ገዢ በነበሩት ዶ/ር ይናገር ደሴ ምትክ የኢትዩጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ማሞ ምሕረቱ ተመድበዋል፡፡


የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩትና በቅርቡ አምባሳደር ሆነው በተመደቡት አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ምትክ ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ ተሹመዋል፡፡


የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ኃላፊነታቸው በሚኒስትር ማዕረግ ሆነው ተሹመዋል፡፡


በመንግስታቱ ድርጅት የኢትዩጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ፅ/ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ መለሰ አለሙ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዘርፍ አስተባባሪ ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።


በሌላ በኩል በአቶ መለስ አለሙ ምትክ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የጥናትና ፐብሊኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ የነበሩት አቶ ሞገስ ባልቻ በከንቲባ አዳነች አቤቤ ተሹመዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


bottom of page