top of page

ጥር 12፣ 2015- ሩሲያ ውስጥ ስለላ ሲያቀላጥፍ ነበር የተባለ አሜሪካዊ ተይዞ መታሰሩ ተሰማ


ሩሲያ ውስጥ ስለላ ሲያቀላጥፍ ነበር የተባለ አሜሪካዊ ተይዞ መታሰሩ ተሰማ፡፡


ሲሰልል ነበረ የተባለው አሜሪካዊ በምህፃሩ FBS ተብሎ በሚጠራው የሩሲያ የደህንነት አካል መያዙን አናዶሉ ፅፏል፡፡


አሜሪካዊው በደፈናው ሥነ ሕይወታዊ ስለላዎችን ሲያከናውን ነበር ተብሏል፡፡


ጉዳዩ በዝርዝር አልተጠቀሰም፡፡


የግለሰቡ ስም በዘገባው አልተነሳም፡፡


ግለሰቡ የተያዘው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ባለፉት 30 ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በእጅጉ በደፈረሰበት ወቅት ነው፡፡


የግንኙነት መደፍረሱ በተለይም የዩክሬይኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ በእጅጉ እየተባባሰ መምጣቱን ዘገባው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page