top of page

ጥር 10 2017 - ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ምቹ ነውን?

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈሱ የውጭ ባለሀብቶች አሁንም በብዛት ወደ ሀገር እየገቡ መሆኑን ይናገራል፡፡


በሌላ በኩል ግን የሀገር ቤት ባለሀብቶችም በቀጠለው የፀጥታ መደፍረስ እና በተለያዩ የታክስ ህግጋት ምክንያት ለስራ አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ሲናገሩ ይደመጣል፡፡


የኢንቨስትመንት አማካሪዎችና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም የማይዋዥቅ የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፀና ሰላም ለሚፈልገው የኢንቨስትመንት ዘርፍ አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ምቹ አይደለም ይላሉ፡፡ እንዲስተካከልም ይጠይቃሉ፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page