የሀገር ኢኮኖሚ የሚበረታው የግለሰቦችም ምርታማነት የድምር ውጤት ታክሎበት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ በተለይ በንግዱ ዘርፍ ለተሰማሩት የፋይናንስ አቅርቦት አስፈላጊ ቢሆንም የብድሩ ተጠቃሚ የሚሆኑት ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡
አነስተኛ ገቢ ያላቸውን፣ ገበሬውን፣ የፈጠራ ስራ ባለቤቶችን ለማበርታት ያለመያዣ ጭምር ብድር እንሰጣለን የሚሉ ባንኮች ቢኖሩም ተግባራዊነቱ ግን ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነው፡፡
ያለ መያዣ የሚሰጠው ብድር ከ5,000 እስከ 10,000 ብር ሲሆን የብር የመግዛት አቅም በእጥፍ ወድቆ በ10,000 ብር ምን ልንነግድበት ነው? ሲሉ ተጠቃሚዎቹ ይጠይቃሉ፡፡
ንጋቱ ሙሉ
Comments