top of page

ግንቦት 9፣2016 - ቴክኖ ሞባይል በቅርቡ በባርሴሎናው ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ቴክኖ ሞባይል አዲሱን እና በቅርቡ በባርሴሎናው ዓመታዊ የቴከኖሎጂ ኤግዚቢሽን ይፋ ያደረገውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በይፋ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ።


አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴከኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴከኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ መሆኑ ተነግሮለታል።


ቴከኖ በቅርቡ በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው አመታዊው የቴከኖሎጂ ኤግዚቢሽን ላይ ይህን አዲስ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴልን ጨምሮ የተለያዩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ምርቶቹን በይፋ እንዳስተዋቀ ይታወሳል።


ቴክኖ ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በማንኛውም አይነት ሁኔታ እና የብርሃን መጠን ሳይገድበው ቁልጭ ያሉ ፎቶዎችን የማንሳት አቅም እንዲኖረው ተደርጓል።


ለዚህም ሲባል በካሜራ ቴክኖሎጂ አንጋፋው ሶኒ (SONY) ምርት የሆነውን ዘመናዊ ሴንሰር (Sony IMX890) ተገጥሞለታል።

በኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ፖላርኤስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የቪድዮ ኢሜጂንግ ሲስተሙን በማዳበር እና እንከን የለሽ በማድረግ የካሜራ ቴከኖሎጂውን ሁለቱ ኩባንያዎች ወደ ላቀ ደረጃ አድርሰውታል ተብሎ ሲነገር ሰምተናል።


ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እየሰጠ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴከኖሎጂ ውጤት የሆኑ የሞባይል ስልከ ግብዓቶችን አካቶ የያዘ ነው መሆኑ ተነግሯለታል፡፡


የቴክኖ ሞባይል ኢትዮጲያ ብራንድ ማናጀር የሆኑት ሚስተር አሌክ ሁዋንግ ‘’ካሞን 30 ፕሮ 5G ስልክ ዘመኑ በደረሰበት ቴከኖሎጂ ውጤቶችን ከኤ አይ ሲስተም ጋር በማስተሳሰር አዳዲስ ፈጠራዎችን ያቀረበ ሲሆን ይህም ቴክኖ እንደ ብራንድ በኢንደስትሪው ግንባርቀደም ለመሆን እየሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው'' ብለዋል።


ቴክኖ የሞባይል ቴከኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌከትሮኒክስ ብራንድ አምራች ሲሆን ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን ያቀርባል።


ቴክኖ ሞባይል በአዲስ አበባ ከተማ ጎሮ አይሲቲ ፓርክ ባስገነባው ዘመናዊ ፋብሪካ የሚገጥማቸውን ዘመናዊ የሞባይል ስልኮች ለተለያዩ ሀገራት እየላከ ዶላር እያስገኘ እንደሆነ ተናግሯል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comments


bottom of page