top of page

ግንቦት  9፣2016 - ‘’ቢጂአይ ኢትዮጵያ’’ እና ‘’ ፐርፐዝ ብላክ’’ አለመግባባታቸውን በስምምነት መፍታታቸው ተሰማ

ቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል አለመግባባታቸውን በስምምነት ፈተዋል ተብሏል።

 

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለቱ ወገኖች መካከል የተፈፀመውን ስምምነት አፅድቆ ክሱን በመዝጋት እግዱም እንዲነሳ አዟል ሲል ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

 

በስምምነቱ መሰረት ቢጂአይ ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን፤ ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል ተብሏል።

 

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜክሲኮ የሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ  እና ፉብሪካ ለፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ለመሸጥ ጀምሮት የነበረው የሽያጭ ሂደት መቋረጡ ይታወሳል።

 

ሰኔ 2015 ዓ.ም በተፈረመ የቀብድ ውል ስምምነት  ከ 8 ወራት በላይ ፈጅቷል፣ የድርድር ሂደቱን እንዲጠናቀቅ እና በተዋዋይ ወገኖች መካከል የቀረበውን የሽያጭ ውል እንዲፈረም ጥረት ቢደረግም ሳይሳካ ቀርቷል ተብሎ ነበር።

 

የሽያጭ ሂደቱ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን ቢጂአይ ኢትዮጵያ ከተናገረ ብኋላ ፐርፐዝ ብላክ ጉዳዮን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶት ነበር።

 

በዚህም ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለቀብድ የተቀበለው ሂሳብ ታግዶ ቆይቷል።

አሁን ቢጂአይ-ኢትዮጵያ የተከፈለውን የቀብድ ክፍያ ለፐርፐዝ ብላክ የመለሰ ሲሆን ፐርፐዝ ብላክ በፍርድ ቤት የጀመረው ክስም ተቋረጦ እግዱ ተነስቷል ተብሏል።

 

ፐርፐዝ ብላክ ሚክሲኮ ለሚገኘው የቢጂአይ ዋና መስሪያ ቤት ግዢ ቅድመ ክፍያ የፈፀመው የአጠቃላይ ዋጋውን 20 በመቶ ወይንም 1 ቢሊዮን ብር መክፈሉ ይታወሳል።

 

ፐርፐዝ ብላክ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ የሚገኘውን የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ አሸንፎ አንደገዛው አና  ለዚህም 1 ቢሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን መናገሩ ይታወሳል፡፡

 

ፐርፐዝ ብላክ የሜክሲኮውን የቢጂአይ ዋና መስሪያ ቤት እና ፉብሪካ ለመግዛት ጉዞ ጀምሮ የነበረው  ባለ 115 ወለል የከገበሬው ታወር እንዲሁም ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለመዝናኛ እንዲሁም፤ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 6 ሕንጻዎችን ለመገንባት ማሰቡን ተናግሮ ነበር፡፡

 

የቢጂአይን ኢትዮጵያ ሜክሲኮ የሚገኘውን የማምረቻ እና ዋና መስሪያ ቤቱን ለፐርፐዝ ብላክ የሸጠው  በውሃ አቅርቦት ውስንነትና በሎጂስቲከስ ችግሮች ምክንያት ነው ብለው  ዋና ስራ አስፈፃሚው ሄርቬ ሚልሃድ  መናገራቸው ይታወሳል።

 

ኩባንያው ቦታውን ለሌላ ገዢ እንደሚያቀርበው ይጠበቃል።

 

ንጋቱ ሙሉ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page