አዋሽ ባንክ በግሎባል ፋይናንስ መፅሔት ‘’ከኢትዮጵያ ምርጡ ባንክ’’ መባሉን ተናገረ።
ይህም ከ 36 ምርጥ የአፍሪካ ባንኮች አንዱ እንዲሆን እንዳደረገው አስረድቷል።
ምርጫውን ያደረገው ግሎባል ፋይናንስ መፅሔት መሆኑ ተነግሯል።
የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትን ዕድገት በየዓመቱ በመተንተን እና ደረጃቸውን በማውጣት የሚታወቀው ግሎባል ፋይናንስ መፅሔት ለ31ኛ ጊዜ የዘንድሮን የዓለም እና የክፍለ አህጉሮችን ምርጥ ባንኮችን ምርጫ ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ባንክ ሆኖ የመመረጡን ባንኩ አስረድቷል።
ባንኩ ይንን ክብር ሲያገኝ የአሁኑ ለተከታታይ 3ኛ ጊዜ ከመሆኑም በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ብቸኛው ባንክ ያደርገዋል ተብሏል።
መፅሔቱ የምርጥ ባንክነትን ደረጃ የሚሰጠው ባንኮቹ ያስመዘገቡት ውጤት በተለይም በትርፋማነት፣ በሃብት ዕድገት በተደራሽነት፣ ባሳዩት ውጤታማ ስልታዊ (Strategic) አመራር፣ በተመዘገቡ አዳዲስ የገበያ ማስፋፋትና የፈጠራ ሥራዎች መዝኖ መሆኑ ተነግሯል።
በተጨማሪም ምርጫው የትላልቅ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎችን፣ ታዋቂ አማካሪዎችን እንዲሁም የባንክ ባለሙያዎችንና የዘርፉ አጥኚዎችን አስተያየት ከግምት ያስገባ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
የምርጫው ውጤትና የአሽናፊዎቹ ዝርዝር በዚሁ ወር በግሎባል ፋይናንስ መጋዚን ላይ እንደሚወጣ ተነግሯል፡፡
ግሎባል ፋይናንስ መጋዚን እ.ኤ.አ. በ1987 ዓ.ም. የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በ193 ሀገሮች ከ 50,000 በላይ ለሆነ አንባቢያን ተደራሽ የሆነ መፅሔት ነው፡፡
አዋሽ ባንክ ከ12.1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች፣ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ 215 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የተሰጠው የብድር መጠንም ብር 178 ቢሊዮን በላይ ደርሷል ብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments