ግንቦት 7 2017 - በብቸኝነት በትግራይ ውስጥ ለአንድ ትውልድ ላላነሰ ጊዜ በበላይነት የቆየው ሕወሓት በህጉ መሰረት ተሰርዘዋል መባሉ በክልሉ ምን ሊያጣ ይችል ይሆን?
- sheger1021fm
- May 15
- 1 min read
የትግራይ ህዝብንና የክልሉ ፖለቲካ ብቸኛ ተጠሪ እና ወኪል ነኝ ሲል የነበረውና ከ40 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ክልሉን ሲያስተዳድር የነበረው ሕወሓት ትናንትና ህጋዊ ሰውነቱን ማጣቱ ተነግሯል፡፡
የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕ.ወሃት) ከፓርቲነት መዝገብ የተሰረዘው በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲሆን ህጋዊነቱን የሚያረጋግጡ ስራዎችን ሰርቶ ለቦርዱ እንዲያቀርብ ሕወሓት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ባለመሆኑ በልዩ ሁኔታ የተመዘገበበት ህጋዊነቱ እንዳበቃ ቦርዱ ተናግሯል፡፡
በብቸኝነት በትግራይ ውስጥ ለአንድ ትውልድ ላላነሰ ጊዜ በበላይነት የቆየው ሕወሓት በህጉ መሰረት ተሰርዘዋል መባሉ በክልሉ ምን ሊያጣ ይችል ይሆን? ስንል በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎችን አስተያየት ጠይቀናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Comentários