የግርብርና ሚኒስቴር የአፈር ማዳበርያ ግዢ ባለፈው ዓመት በወቅቱ ባለመግዛቱ ሀገሪቱ 100 ሺህ ዶላር ተጨማሪ እንድታወጣ አድርጓታል ተብሏል፡፡
ይህንን የተናገሩት የግብርና ሚኒስትሩ ናቸው፡፡
ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማቸው የ9 ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፤ የአፈር ማዳበሪያ ግዢን አሰራር በዚህ አመት በመሻሻሉ እና በጊዜው በመገዛቱ 21 ቢሊየን ብር ማዳን ተችሏል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ባለፈው አመት ለአፈር ማዳበሪያ ግዢ ያወጣው 1 ቢሊየን 54 ሚሊየን ዶላር ሲሆን የገዛው 13.6 ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ነው፡፡
በዚህ አመት 930 ሚልየን ዶላር በበመደብ የ6 ሚልየን ኩንታል ብልጫ ያለው 19 ነጥብ 4 ሚልየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ገዝቷል፡፡
ከተገዛው ማዳበሪያ ውስጥ 11 ሚልየን ኩንታል የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል ብለዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር በየጊዜው የሚነሱ ተባዮችን ለመከላከል 5 አውሮፕላኖችን ግዢ አድርጓል ያሉ ሲሆን አውሮፕላኖቹ አሁን ላይ ለስራ ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡
አውሮፕላኖቹ እርጭትና ቅኝት ለማድረግ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ለማረፍና ለመነሳት የሚያስችላቸው ስፍራዎች አለመዘጋጀታቸውን ተነግሯል፡፡
ይህንን አገልግሎት እያገኙ ያሉት መደበኛ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ሲሆን አንዳንድ ስፍራዎች ስራው ከሚሰራበት ስፍራ ርቀት እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
የአፈር ለምነቱን አሲዳማ አፈርን ለማከም የሚያስችልና ምርጥ ዘርን በብዛት ለገበሬው ለማቅረብ የሚያስችል የ3 አመት ፍኖተ ካራታ ይፋ ተደርጓል ብለዋል ዶክተር ግርማ፡፡
ከዚህ ባለፈ ባለፉት ጊዜያት በተሰራ ስራ የሀገሪቱ የደን ሽፋን እንዲያድን አስችሏል ያሉ ሲሆን አሁን ላይ የደን ሽፋኑ 17 ከመቶ ደርሷል አዲሱ የደንሽፋን መረጃ ሰኔ ላይ ይፋ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር በበጋ የስንዴ መስኖ ልማት 80 ኩንታል ምርት እስካሁን ተሰብስቧል ያለ ሲሆን ቢያንስ ከዚህ አመት እስከ ከአንድ መቶ ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ከበጋ መስኖ ልማቱ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
የግብርናው ዘርፍ በየአመቱ ከ2 ቢልየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ያስገኛል የሚሉት ሚኒስትሩ በዚህ አመት ከቡና መላክ ብቻ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ይገኛል የሚል እምነት እንዳለ መናገራቸው ሰምተናል፡፡
ሰፋፊ እርሳችን ለማስፋፋት በማሰብ የኩታ ገጠም ግብርና ስራን እየተስፋፋ ነው የተባለ ሲሆን አሁን ላይ 6.8 ሚልየን ሄክታር መሬት በዚህ መንገድ እየታረሰ መሆኑን ተነግሯል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments