ከ 300 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 11 ዋና ዋና ያሏቸውን አጀንዳዎች አስረከቡ፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይታይልን ያሉትን 11 አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ ያስረከቡት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በኩል ነው፡፡
በሀገሪቱ በሁሉም ክልሎች ከሚገኙ ከ300 በላይ የሚሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረቡ አጀንዳዎች ናቸው ለኮሚሽኑ የተሰጡት፡፡
አጅዳዎቹ የህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳይ የሀብትና የስልጣን ክፍፍል ጉዳይ፣ የተለያዩ የታሪክ አረዳድና ትርክቶች ጉዳይ፣ ዘለቄታዊ የሰላም ግንባታ ጉዳይ ይገኙባቸዋል፡፡
የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀር ጉዳይ፣ የመሬት ስሪትና አጠቃቀም ጉዳይ፣ ዘለቄታዊ የተቋማት ሥርዓት ዝርጋታ ጉዳይ ፣ ነባር አገራዊ እሴቶችን ማበልፀግና የመጠቀም ጉዳይ፣ የፖለቲካዊነት የመስተጋብር ጉዳይ፣ የፖለቲካ ባህል ጉዳይ፣ የተጋላጭ ዜጎች ወይንም ሴቶች፣ ወጣቶች ሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞችና የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጉዳይ በምክክሩ በአጀንዳነት እንዲነሱ በተመረጡ መካከል መሆናቸውን የተናገሩት የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሐና ወ/ገብርኤል ናቸው፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments