ከውጭ በዶላር ተገዝቶ ወደ ሀገር የገባ ከፍተኛ መጠን ያለው የአፈር ማዳበሪያ የግብርና ሚኒስቴር በተገቢው ጊዜ ማሰራጨት አልቻለም ተባለ፡፡
ከውጭ የገባ የአፈር ማዳበሪያም ለአርሶ አደሮች ሳይሰራጭ በየዩኒየኖች እና በየህብረት ስራ ማህበራት መጋዘኖች ተከማችቶ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
በእዚህም ከውጭ ተገዝቶ ከገባ እና ለአርሶ አደሮች መሰራጨት ከነበረበት 15.9 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ የተሰራጨው 2.5 ሚሊዮኑ ብቻ ነው ተብሏል፡፡
ይህን የሰማነው የግብርና ሚኒስቴር በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተገኝቶ የ9 ወር የስራ ክንውን ሪፖርቱን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ነው፡፡
የፀጥታ ችግር የተከሰተበት የአማራ ክልል ላይ የማዳበሪያ ስርጭቱ አፈፃፀም ጥሩ እንደሆነ የግብርና ሚኒስቴር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል በዘንድሮ ዓመት እስካሁን ምንም አይነት የአፈር ማዳበሪያ ያልደረሰባቸው አካባቢዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
ባለፉት 9 ወራት በአሲድ የተጠቃ 300,000 ሄክታር መሬት በኖራ ለማከም ቢታቀድም ማከም የተቻለም ግን 3.355 ሄክታር መሬት ብቻ ነው ተብሏል፡፡
የምርጥ ዘር አቅርቦትም ዝቅተኛ አፈፃፀም ማስመዝገቡም በቋሚ ኮሚቴው ተነስቷል፡፡
ባለፉት 9 ወራት 900,000 ምርጥ ዘር ለማቅረብ ቢታቀድም የቀረበው ግን 342,000 ወይም የእቅዱን 38 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡
የውጭ ምንዛሪ የሚገኝባቸው የወጪ ምርቶች አፈፃፀምም 68 በመቶ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments