top of page

ግንቦት 6 2017 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ አወጣለሁ ማለቱና ስራ ላይ ማዋሉም ይታወቃል፡፡

  • sheger1021fm
  • May 14
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ መደበኛ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ ጨረታ አወጣለሁ ማለቱና ስራ ላይ ማዋሉም ይታወቃል፡፡


ይህም የማዕከላዊ ባንኩ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት ለማሳካት ነው ተብሏል።


ለመሆኑ የዚህ የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የጨረታ ተሳትፎ ገበያው እያረጋጋው ነው ወይ?


ውጤትስ ተገኝቶበታል ወይ? ስንል የንብ ባንክ ፕሬዘዳንትን አቶ ሔኖክ ከበደን ጠይቀናል።

ባንኮች አንዳንዴ የብሔራዊ ባንክ በሚያቀርበው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በብዛት ይሳተፋሉ፤ የሆነ ወቅት ደግሞ ከግማሽ በታች ይሳተፋሉ፤ የሆነው ሆኖ ለገበያው ምን እፎይታ ሰጠ?


አቶ ሔኖክ ለባንኮች በቂ የውጭ ምንዛሪ እየቀረበ መሆኑን አስረድተው፤ ለደንበኞችም በሚፈልጉት መጠን እየቀረበ ነው ይላሉ።


በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲነግሩን የጠየቅናቸው ፋይናንስ ባለሙያ በበኩላቸው በቋሚነት በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ጨረታው መውጣቱ በጎ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ግን እስካሁን በጥቁር ገበያው ላይ ተፅእኖ እያሳደረ አይደለም ብለውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page