top of page

ግንቦት  6፣2016 - የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ ተፈፀሞበታል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • May 14, 2024
  • 1 min read

የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ ተፈፀሞበታል ተባለ፡፡


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ዝርፊያ እንደተፈጸመበት ተነግሯል፡፡


በፖሊስ ጣቢያው ዝረፊያ የተፈፀመው ትናንት ሰኞ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም  ከምሽቱ 7፡40 ገደማ ነው ተብሏል፡፡


በዝርፊያው ለጊዜው ተለይተው ያልታወቁ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ከፖሊስ ጣቢያው እንደተወሰዱ የወልቂጤ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ትዕግስቱ ፉጅየ ነግረውናል፡፡


በተጨማሪም ከጣቢያው ተዘርፎ የነበረ ፓትሮል መኪና መንገድ ላይ ተገኝቷል ብለውናል፡፡


በአሁን ሰዓት ፖሊስ ጣቢያው ታሽጎ የማጣራት ሂደት እየተከናወነ እንደሆም ሰምተናል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page