top of page

ግንቦት  6፣2016 - ባለፉት 80 ዓመታት ቅርስን ከመመዝገብ እና ከመጠበቅ ባለፈ በምርምር ዘርፉ ላይ የተሰራው ስራ አነስተኛ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • May 14, 2024
  • 1 min read

ባለፉት 80 ዓመታት ቅርስን ከመመዝገብ እና ከመጠበቅ ባለፈ በምርምር ዘርፉ ላይ የተሰራው ስራ አነስተኛ ነው ተባለ፡፡


የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ቅርሶች ላይ ያተኮረ የቅርስ ምርምር ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ እያካሄደ ነው።

 

ባለስልጣኑ ባለፉት 80 ዓመታት ቅርስን ከመመዝገብ እና ከመጠበቅ ባለፈ በምርምር ዘርፉ ላይ የሚሰራው ስራ አነስተኛ ነበር የተባለ ሲሆን፤ አሁን ላይ ግን ዋንኛው ትኩረቱ በሀገር ውስጥ ባለሞያዎች ጥናቶችን እያደረገ ነው ተብሏል።

 

ከዚህ ቀደም አባዛኛው ጥናቶች ይደረግ የነበረው በሌሎች ሀገራት ሰዎች እንደነበረም በመድረኩ ተነሰቷል፡፡

 

 በአሁኑ ጥናቶች ግን የሀገር ውስጥ ባለሞያዎች በዘርፉ የተሻለ ትምህርት እንዲማሩ እና ብቁ እንዲሆኑ ተደርጓል መባሉንም ሰምተናል፡፡

 

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ቅርሶችን በአግባቡ በመጠበቅ ለምርምር እና ህብረተሰቡ እንዲያውቃቸው መድረግ እንዳለበት የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ሽኩር ተናግረዋል።

 

ባለስልጣኑ አሁን ዋንኛ ትኩረቱ ቅርስ ላይ ምርምር ማድረግ ነው ያሉት አቶ ኤልያስ፤ ይህም አዳዲስ የአርኪዮሎጂ ቁፋሮን ጨምሮ እስከ ቅርስ እድሳት ድረስ ያሉ ስራዎች በራስ ባለሞያዎች ለመስራትና ለመጠበቅ ያስችላል ብለዋል።

 

የቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በርካታ ቅርስ ቢኖራትም እስካሁ ድረስ አልምታ ለገብያ ባለማቅረቧ የሚገባትን ያህል ገቢ ከዘርፉ እንዳታገኝ አድርጓታል ሲሉ ተናግረዋል።

መንግስት አሁን ላይ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ቅርሶች ባሉባቸው አካባቢዎች መሰርተ ልማቶችን ለማሟላት እየሰራ ነው ብለዋል።

 

ዘርፉ የተሻል እድገት እንዲያሳይ የምርምር ስራዎች መስራት ትልቅ ጥቅም አለው የተባለ ሲሆን የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ ብኋላ በስሩ ባሉት የምርምር ባለሙያዎች በመጠቀም ሰፊ ስራ ለመስራት ማቀዱን ሰምተናል።

 

ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ አመታዊ የቅርስ ምርምር ጉባኤ እስከ መጪው አርብ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በዘርፉ ላይ የተሰሩ ጥናትና ምርምሮች ይቀርቡበታል ተብሏል።

 

 በረከት አካሉ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page