የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ 26,900 በላይ ቅሬታዎችን ተቀበልኩ አለ፡፡
በ2016 በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ በ1,454 አቤቱታ መዝገቦች ስር 26,912 ሰዎች የአስተዳደር በደል ተፈፅሞብናል ያሉ አቤቱታ አቅራቢዎችን በደል መቀበሉን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ተናግሯል፡፡
ተቋሙ በዘጠኝ ወሩ ለመስራት ካቀደው መሳካት የቻለው 51 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡
ይህ ማለትም በዘጠኝ ወራት ውስጥ 2 ሺህ 823 አቤቱታ መዝገቦች ለመቀበል አቅዶ መቀበል የቻለው 1 ሺህ 454 እንደሆነ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው ፅሁፍ አስረድቷል፡፡
ምክንያቱ ደግሞ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ነፃ የጥሪ ማዕከል ከተቋሙ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ለሰባት ወራት ያክል በመቋረጡ እና በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ነው ተብሏል፡፡
ከአቤቱታ አቅራቢዎች ውስጥ 7 ሺህ 376 ወንዶች፣ 3 ሺህ 284 ሴቶች እንዲሁም 15 ሺህ 654 ያልተለዩ ፣ በድምሩ 26 ሺህ 9 መቶ በላይ ሰዎች አቤቱታ ማቅረባቸው መናገሩ ተሰምቷል፡፡
ለተቋሙ አቤቱታዎች የቀርቡባቸው መንገዶች፤ በአካል 1,204 (82.8%)፣ በስልክ 1,021(8.3%)፣ በፖስታ 33(2.2%)፣ በፋክስ 1፣ በኢሜልና ቴሌግራም 25(2%)፣ በጥሪ ማዕከል 17(1.5%) እና በልዩ ልዩ መንገዶች 52(3.5% ) በድምሩ 1,454 (100 %) አቤቱታ መዝገቦች መቅረባቸው ተነግሯል፡፡
በሀገሪቱ ያለው አለመረጋጋት የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመላ ሀገሪቱ ተንቀሳቅሶ መስራት እንዳይችል እንዳረገው ለሸገር መናገሩ ይታወሳል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários