ግንቦት 4፣2017 - ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የDHL ኢትዮጵያ ሰራተኞች ነገ ወደ ስራ ለመመለስ ተስማምተናል አሉ፡፡
- sheger1021fm
- May 13
- 1 min read

ግንቦት 4፣2017
ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የDHL ኢትዮጵያ ሰራተኞች ነገ ወደ ስራ ለመመለስ ተስማምተናል አሉ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ እና የትራንስፖርት እና መገናኛ ሰራተኞች ማህበር ፌዴሬሽን ጣልቃ ገብተው በማሸማገል የሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ እገዛ ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡
ለኢንዱስትሪ ሰላም ሲባል በተቋሙ ላይ ግፊት አድርገንም ጭምር ለጊዜው የ35 በመቶ ደመወዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ አግባብተን አስማምተናቸዋል ሲሉ የቦሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ሰላምና የሙያ ደህንነት ፤ ጤንነት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ማንደፍሮ ስዩም ነግረውናል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments