top of page

ግንቦት 4 2017በዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ኢትዮጵያውያኑ የተከራከሩበትና ኢትዮጵያ የተጠየቀችበት የአንድ ቢሊየን ዶላር የካሣ ክፍያ አብዛኛው ውድቅ ሆነ፡፡

  • sheger1021fm
  • May 13
  • 1 min read

የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ ገበያ የባቡር መስመር እንዲገነባ ከተዋዋለው የቱርክ የስራ ተቋራጭ ፣ ክስ ቀርቦበት ነበር፡፡


የቱርክ የሥራ ተቋራጭ ፣ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ስራው በመስተጓጎሉና በመዘረፉ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አንድ ቢሊዮን ዶላር ካሣ እንዲከፍለው ክስ አቅርቧል፡፡


ኮርፖሬሽኑም ለንደን በሚገኘው ፣ በአለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት የሚከራከሩ ባለሙያዎች ለማግኘት ጨረታ አውጥቶ ፣ የህግ ባለሙያውን ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመን መርጦ እንዲከራከሩ አድርጓል፡፡


በረዳትነትም የኮርፖሬሽኑ የህግ ክፍል ተሳትፏል፡፡


የቱርክ ሥራ ተቋራጭ በርካታ የክስ ዓይነቶች ያቀረበ ሲሆን ለነዚሁም ከ800 በላይ ማስረጃዎቹን አቅርቧል፡፡


ኢትዮጵያውያን፣ በብቸኝነት ተከራክረው በማያውቁበት አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ብቸኛ ተከራካሪ ሆነው የቀረቡት፣ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣ በክሶቹ ላይ መልስ የመልስ መልስ በመስጠት ተከራክረዋል፡፡


በእንግሊዘኛ በተፃፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ገጾች በሚደርሱ የክርክር ሀሳቦች፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቀርበው ተከራክረዋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ለሁለት አመታት ሲያይ የሰነበተው አለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት፣ ኢትዮጵያ ከቀረበባት አብዛኛውን የካሣ ጥያቄ ልትከፍትል አይገባትም ብሎ መወሰኑ ሰምተናል፡፡


በውሳኔ ትንታኔ፣ ላይ ከስራው በፊት ኢትዮጵያ በዶላር የከፈለችው ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆንላት ወስኗል፡፡


ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ጉዳት ሲያስከትል የሚችለውን የካሣ መጠን ፣ ኢትዮጵያውያኑ ባለሙያዎች ተከራክረው ማስቀረታቸው በአለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ብዙ ጊዜ አሸንፋ ለማታውቀው ኢትዮጵያ ብቁ ባለሙያዎች እያፈራች መሆኑን የሚያመለክት ነው ተብሏል፡፡


ባለፈው ሐሙስ ዘገባችን፣ በክርክሩ ላይ እንግሊዛውያኑ የህግ ባለሙያዎች መቀጠራቸውና እነ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ በተባባሪነት እንደቀረቡ ተደርጎ የተሰጠው ቃለ መጠይቅ ስህተት በመሆኑ በዚህ እንዲታርም ሸገር ከይቅርታ ጋር ያስታውሳል፡፡


እሸቴ አሰፋ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page