የሀብት ብክነት እና ዘረፋን ጨምሮ የተለያዩ ችግሮች ይታይባቸዋል የተባሉ የህብረት ስራ ማህራትን ዳግም ለማደራጀት(ሪፎርም) ለማድረግ ስራ መጀመሩ ይታወሳል።
ከማህበራቱ ብዛት አንጻር ግን በትክክል እየሰሩ የሚገኙትን ከሌሉት መለየቱ በራሱ ጊዜ ጠይቋል ተብሏል።
በአምራቾችም፣ በሸማቾችም የተቋቋሙ የህብረት ስራ ማህበራት ጥራት ያላቸው ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ፤ ገበያው ላይ እንዲገኙ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ይነገራል።
የዚያኑ ያህል ግን የተለያዩ ችግሮች እንዳሉባቸው ይነሳል።
የብቃት እና ተወዳዳሪነት ማነስ ፤ የሃብት ብክነትና ዘረፋ እንዲሁም የፋይናንስ እጥረት ከችግሮቹ መካከል እንደሆኑ የኢትዮጵያ የህብረት ስራ ኮሚሽን ይጠቅሳል።
እነዚህን እና መሠል የማህበራቱን ችግሮች ለመፍታት ዘርፉን ሪፎርም ማድረግ እንዳስፈለገ ኮሚሽኑ ባለፈው ታህሳስ ወር ይፋ አድርጎ ነበር።
ሪፎርሙ የህብረት ስራ ማህበራቱ ጠንካራ አደረጃጀት እና አመራር እንዲኖራቸው ያስችላል ነው የተባለው።
የገበያ ድርሻቸውን እና ተጽዕኗቸውን የሚያሳድግ እንደሚሆንም ተጠቅሷል።
የፋይናንስ ችግራቸውን ለመፍታት የህብረት ስራ ባንክ እንደሚቋቋም ፤ በሂደት ደግሞ አገር አቀፍ ''የህብረት ስራ ሊግ'' እንደሚደራጅ በጊዜው ተነግሯል።
ለመሆኑ ማህበራቱን ሪፎርም የማድረጉ ስራ ከምን ደርሷል?
Comments