የድንቅነሽ፣ የሰላም ቅሪተ አካል መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ የሰው ልጅ አመጣጥን የሚያሳይ ሙዚየም ልትገነባ ነው፡፡
ይህንን ያለው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በአርኪዮሎጂ ቁፋሮ በተገኙ መረጃዎች መሰረት የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ይነገራል፡፡
ሀገሪቱ ላይ ይህንን የሚያሳይ ሙዚየም ለመገንባት እየተዘጋጀሁ ነው፤ ያለው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ሙዚየሙ ከሰው ልጅ አመጣጥ ጋር የተያያዙ ቅርሶች ብቻ እንዲይዝ ይደረጋል ብሏል፡፡
የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ለሙዝየሙ ግንባታ የሚሆን ቦታ እየተዘጋጀ መሆኑንም የነገሩን ሲሆን በ10 ዓመቱ እቅድ ሳይጠናቀቅ ለመፈፀም ታቅዷል ሲሉ ነግረውናል፡፡
በሌላ በኩል የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የ’’ሞአ አንበሳ ሐውልት’’ አሁን ካለበት ስፍራ 50 ሜትር ገባ አድርጎ እንዲቀመጥ ለማድረግ እየተዘጋጀሁ ነው ብሏል፡፡
የሞአ ሀውልት በጣልያን ጊዜ ከተዘረፉ ቅርሶች መካከል አንዱ እንደነበርም የሚታወስ ሲሆን ሀውልቱ አሁን የቆመበት ስፍራ መንገድ ስለሚነካው ነው ካለበት ስፍራ ገባ ተደርጎ እንዲያርፍ የተፈለገው ተብሏል፡፡
አዲስ አበባ ላይ ከዚህ በፊት ተሰርተው የነበሩ አንዳንድ ሀውልቶች በተለያዩ ጊዜያት ከቆሙበት ስፍራ ሲነሱ ይስተዋላል ለአብነትም የቦብ ማርሊ፣ ፑሽኪን እና ካርል ሀውልቶች ይጠቀሳሉ፡፡
Comments