በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን እና በመዝገቡ የሚገኙ ተከሳሾች ወደ ማረሚያ እንዲወርዱ ፍ/ቤት አዘዘ፡፡
ቀሲስ በላይ መኮንን እና በክስ መዝገቡ ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
በክስ መዝገቡ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያሉ ተከሳሾች ችሎት የቀረቡ ሲሆን 4ኛና 5ኛ ተከሳሾ አልቀረቡም፡፡

ችሎቱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሽልላቸው ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ እና ዘግይተው የዋስትና ጥያቄ ባቀረቡት 3ኛ ተከሳሽ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
በዚህም ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሽላቸው ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ በማስረጃ እንዲጣራ በማለት ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል፡፡
ከሳሽ አቃቤ ህግ ምስክሮችን ለማቅረብ ባቀረበው ጥያቄ ፍ/ቤቱ የምስክሮችን ቃል ለማድመጥ ለሰኔ 26 እና 27 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ችሎት ያልቀረቡትን 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በተመለከተ ፖሊስ 4ኛ ተከሳሽ አሉበት የተባለው ቦታ የጸጥታ ችግር ያለበት በመሆኑና 5ኛ ተከሰሽ ደግሞ በአድራሻቸው አለመገኝታቸውን ጠቅሶ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ፍ/ቤቱን ጠይቋል፡፡
ፍ/ቤቱም ፖሊስ በአካባቢው የጸጥታ ችግር ስለመኖሩ ማረጋገጫ እንዲያቀርብና 5ኛ ተከሳሽን አድራሻ አጣርቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ
ሰጥቷል፡፡
Comments