top of page

ግንቦት 29፣2016 - ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተክርስቲያን በሚደረጉ ስብከቶች እና ትምህርቶች ላይ ከሀይማኖት ትምህርት ውጪ መምህራንና አባቶች እንዳያስተምሩ ከለከለ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርትስቲያን ፓትሪያሪክ ብፅዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሀገሪቱ ውስጥ ጦርነት እያደረጉ ያሉ አካላት ግጭቶችን በማቆም ችግራቸውን በንግግር ሊፈቱ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡


ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዟል።


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርትስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት ሲያካሄደው የነበረው የግንቦት እረክበ ካህናት ጉባኤ የተጠናቀቀ ሲሆን 12 ጉዳዮች ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች በተለመከተ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡


ቅዱስ ሲኖዶስ ከተወያየባቸው ጉዳዮች መከከል የሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ አንዱ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ በረቂቅ አዋጁ ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ብሎ ያመነባቸውን የማሻሻያ ሐሳቦች በማዘጋጀት ለሚመለከተው መንግሥታዊ ተቋም እንዲላክና ረቂቅ አዋጁ ከመጽደቁ በፊት የተሰጡት የማሻሻያ ሐሳቦች በረቂቁ ስለመካተታቸው ክትትል የሚያደርግ ኮሚቴም ሰይሟል፡፡


ግብረ ሰዶማዊነትና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ፣በመፅሐፍ ቅዱስም ፈጽሞ የተከለከለ ፣በቀኖናተ ቤተ ክርስቲያን ፣በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች በሥነ ልቦና ደንቦች የተወገዘ ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ ግለሰባዊ ማንነትን፣ ቤተሰባዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚጎዳ ነው ሲል ሲኖዶሱ ገልፆታል ።


በቤተክርስቲያን ስብከቶች ላይ ከሀይማኖት ትምህርት ውጪ መምህራንና አባቶች ማስተማር በተለይም ግጭትን የሚቀሰቅሱ ስብከቶችን እንዳያስተላልፉ፣ ቤተክርስቲያኗም ከዚህ በኋላ እንደማትታገስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡


በረከት አካሉ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page