ግንቦት 28 2017 - የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መንግስት ረቂቅ አዋጅ አሰናድቻለሁ አለ፡፡
- sheger1021fm
- Jun 5
- 1 min read
ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ #የገቢ_ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ ተሰናድቷል፡፡
በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉን ሰምተናል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተለይ ቋሚ ደመወዝተኛው የኑሮ ጫናውን ለመቋቋም እንዲችል የሚቆረጥበት የገቢ ግብር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሻሻልለት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

ባለሞያዎች የደመወዝ የገቢ ግብር ይሻሻል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር በንፅፅር ይናገራሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብር እና የኬንያ ሽልንግ ከዶላር አንፃር የምንዛሪ ዋጋቸው እኩል ነው፡፡
በኢትዮጵያ ከ600 ብር ጀምሮ የሚያገኝ ደመወዝተኛ የገቢ ግብር ይቆረጥበታል፤ በኬንያ ደግሞ የገቢ ግብር የሚቆረጠው ከ24,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ደመወዙ 10,900 ብርና ከዚያ በላይ የሆነ ተቀጣሪ 35 በመቶ የገቢ ግብር ሲቆረጥበት፤ በኬንያ ከ800,000 ብር ደመወዝተኛ ጀምሮ ነው 35 በመቶ የገቢ ግብር የሚቆረጥበት፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments