top of page

ግንቦት 28 2017 - የባህር ማዶ ወሬዎች

  • sheger1021fm
  • Jun 5
  • 2 min read

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ12 አገሮች ዜጎች ወደ አገራችን ድርሽ እንዳይሉብን አሉ፡፡


በፕሬዘዳንቱ አዲስ ትዕዛዝ መሰረት የአፍጋኒስታን ፣ የቻድ ፣ የኮንጎ ፣ የኢኳቶሪያል ፣ ጊኒ ፣ የኤርትራ ፣ የሔይቲ ፣ የኢራን ፣ የሊቢያ ፣ የማያንማር ፣ የሶማሊያ ፣ የሱዳን እና የየመን ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እንደተከለከሉ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


የቡሩንዲ ፣ የኩባ ፣ የላኦስ ፣ የሴራሊዮን ፣ የቶጎ ፣ የቱርክሜንስታን እና የቬንዙዌላ ዜጎች ደግሞ ከፍተኛ ገደብ የተደረገባቸው እንደሆኑ ታውቋል፡፡

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጉዞ ክልከላ እና ግደባውን ያደረጉት ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ብዬ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ትራምፕ በቀዳሚው የፕሬዘዳንትነት ጊዜያቸውም እንደ ሶማሊያ እና ሱዳን ያሉትን ጨምሮ የ7 አገሮች ዜጎች ድርሽ እንዳይሉብኝ ብለው እንደነበር መረጃው አስታውሷል፡፡


ፕሬዘዳንቱ ከጉዞ ክልላና ገደብ ትዕዛዛቸው በተጨማሪ የውጭ አገራት ተማሪዎች ወደ ሐርቫርድ ዩኒቨርስቲ ለትምህርትም ሆነ ለጥናት እንዳይመጡ መከልላቸው ታውቋል፡፡



የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ ዓሊ ሐሚኒ ዩራኒየም ማበልፀጋችንን በጭራሽ አንተውም አሉ፡፡


አያቶላህ ዓሊ ሐሚኒ ዩራኒየም ማብላላታችንን በጭራሽ አንተውም ያሉት አሜሪካ አቅርባዋለች ለተባለ የመደራደሪያ ሀሳብ በሰጡት ምላሽ እንደሆነ አልጀዚራ ፅፏል፡፡


ሁለቱ አገሮች ኒኩሊየር ነክ ንግግር እያደረጉ ነው፡፡


አሜሪካ ኢራን ዩራኒየም ማብላላቷን ከነአካቴው እንድትተው ትሻለች ይባላል፡፡


የቅርብ ጊዜውም የአሜሪካ የመደራደሪያ ሀሳብ ይሄንኑ ጉዳይ የተመለከተ ነው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡


ምዕራባዊያን ሀያላን ኢራን የኒኩሊየር ቦምብ ለመስራት እየተሯሯጠች ነው ሲሉ ይከሷታል፡፡


ኢራን በበኩሏ መርሐ ግብሯ ለኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ እና ለሰላማዊ አገልግሎቶች የታለመ ነው ስትል ትሟገታለች፡፡


በእጅጉ የተብላላ ዩራኒያም ለኒኩሊየር ቦምብ መስሪያት ይውላል፡፡



የኢንዶኔዥያ የጤና ተቋማት የኮቪድ 19 የወረርሽኝ ቅኝታቸውን እንዲያበረቱ ታዘዙ፡፡


በአሁኑ ወቅት በታይላንድ ፣ በሆንግ ኮንግ፣ በታይላንድ እና ማሌዥያ የኮቪድ 19 ወረርሽን ዳግም እየተዛመተ መሆኑን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


በኢንዶኔዥያም በዝቅተኛ ደረጃም ቢሆን ወረርሽኙ እየተስተዋለ ነው ተብሏል፡፡


ይሁንና በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ብዛት እየጨመረ መምጣቱ ተጠቅሷል፡፡


የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር የጤና ተቋማት የወረርሽኝ ቅኝታቸውን እንዲያሳድጉ ማዘዙ ተሰምቷል፡፡


ኢንዶኔዥያ በአለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኙ ተስፋፍቶ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገዱት አገሮች መካከል አንዷ እንደነበረች ለትውስታ ተጠቅሷል፡፡


በጊዜውም ኮቪድ 19 ኢንዶኔዥያ ውስጥ 160 ሺህ ሰዎችን መጨረሱን መረጃው አስታውሷል፡፡



ብሪታንያ እና ፈረንሳይ ለፍልስጤም ነጻ አገርነት እውቅና እንዳይሰጡ አሜሪካ በብርቱ አስጠነቀቀቻቸው ተባለ፡፡


የፍልስጤምን ነፃ አገርነት በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከ2 ሳምንታት ባነሰ ጊዜ አለም አቀፍ ጉባኤ እንደሚደረግ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡


ሳውዲ አረቢያ እና ፈረንሳይ የአለም አቀፍ ጉባኤው ዋነኞቹ አስተባባሪዎች ናቸው ተብሏል፡፡


ብሪታንያ እና ፈረንሳይ በየፊናቸው ለፍልስጤም ነፃ አገርነት እውቅና ለመስጠት መሰናዳታቸውን እወቁልን ካሉ ሰንብተዋል፡፡


አየርላንድ ፣ ኖርዌይ ፣ ስፔን እና ስሎቬኒያ ከ58 አመታት በፊት በነበረው ድንበር መሰረት ፍልስጤም በነፃ አገርነት የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባል እንድትሆን ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡


እነዚህ ሀገሮች ቀደም ሲል ለፍልስጤም ነፃ አገርነት እውቅና መስጠታቸውን መረጃው አስታውሷል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page