top of page

ግንቦት 28 2017 - ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎችን በሀገር ቤት አቅም ለመደገፍ ከደመወዝተኛው ላይ በየወሩ እንዲቆረጥ የሚያስገድደው ድንጋጌ ተሰረዘ

  • sheger1021fm
  • Jun 5
  • 1 min read

ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎችን በሀገር ቤት አቅም ለመደገፍ ከደመወዝተኛው ላይ በየወሩ እንዲቆረጥ የሚያስገድደው ድንጋጌ ተሰረዘ፡፡


የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር #አዋጅ ዛሬ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡


የአዋጁ ዓላማ አደጋን ቀድሞ ለመከላከልም ሆነ ከደረሰ በኋላ በሀገር ቤት የገንዘብ ምንጭ መቋቋም ነው፡፡


ለዚህም የአደጋ ጊዜ ፈንድ እንደሚቋቋም አዋጁ ይደነግጋል፡፡


ለሚቋቋመው ፈንድም ከተቀጣሪው ከደመወዙ ጭምር በየወሩ እንዲያዋጣ በረቂቁ ተደንግጎ እንደነበር ይታወሳል፡፡


ይህም ከፍተኛ የኑሮ ጫና ያለበትን ደመወዝተኛ ይበልጥ የሚጎዳ ነው በሚል በፓርላማው ጭምር ተቃውሞ ቀርቦበት ነበር፡፡


ዛሬ በፓርላማ አዋጁ ሲፀድቅም ለአደጋ ጊዜ ፈንድ ከተቀጣሪው ደመወዝ ተቆርጦ እንዲያዋጣ የሚለው ድንጋጌ ቀሪ መደረጉን ሰምተናል፡፡


በሌላ በኩል ግን እንደ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና ባንኮች ለአገልግሎት ክፍያ ከሚሰበስቡት ላይ ለአደጋ ጊዜ ፈንዱ ማዋጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡


እንዲሁም ነጋዴው ንግድ ፈቃድ ሲያወጣም ሆነ ሲያሳድስ ለሚቋቁመው የአደጋ ጊዜ ፈንድ በቁርጥ ገንዘብ እንዲከፍሉ አዋጁ ያስገድዳል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page