ግንቦት 28፣2016 - የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ለግሉ ዘርፍ የሀገር ቤት የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ በሩን ከፍቷል
- sheger1021fm
- Jun 5, 2024
- 1 min read
የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ለግሉ ዘርፍ የሀገር ቤት የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ በሩን ከፍቷል።
የግል አየር ትራንስፖርት እንዲሰጡ የተጋበዙት ድርጅቶች እየሰጡት ካሉት የቻርተር በረራ በተጨማሪ መደበኛ የመንገደኞች እና የጭነት በረራ አገልግሎት እንዲሰጡ ነው የተፈቀደላቸው።
ይህ ፍቃድ መሰጠቱ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚን ያሳድጋል፣ ምርትና አገልግሎትን ከ አንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ለማሸጋገር ይረዳል፣ ቱሪዝምን ያሳድጋል ያለው ባለስልጣኑ ነው።
የኢትዮዽያ ሲቪል አቭዬሽን ባለስልጣን ከዚህ በተጨማሪም ይህ ፍቃድ መሰጠቱ የአውሮፕላን የበረራ አገልግሎት ዋጋንም ይቀንሳል ገና ብዙ ያልተነካ ዘርፍ ነው ብሏል።
ሸገር በዚህ ጉዳይ የጠየቃቸው የአቢሲንያ በረራ ድርጅት ሀላፊና መስራች ካፒቴን ሰለሞን ግዛው መፈቀዱ በጎ ቢሆንም ቀድሞ መሰራት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡
ካፒቴን ሰለሞን በ ሐገር ውስጥ የአውሮፕላን ጥገና ለማድረግ አይቻልም ይህን ለማድረግ ወደ ውጭ እንበራለን ይህ ደግሞ ከፍተኛ ወጪና የሀገርም ሀብት ያባክናል ብለዋል፡፡
Comments