ግንቦት 28፣2016 - የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ሆኖ ቀረበ
- sheger1021fm
- Jun 5, 2024
- 1 min read
የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ለሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ሆኖ ቀረበ፡፡
‘’አዲስ አበባ ክልል ትሁን ወይስ አትሁን’’ የሚሉ ጥያቄዎች በምክክር እንዲፈቱ አጀንዳ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
አዲስ አበባን ወከለው በምክክሩ የተሳተፉ ተወካዮች የአዲስ አበባ ባለቤትንት እና የወሰን ጉዳይ መፍትሄ እንዲገኝ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳ አድርገው አቅርበዋል፡፡
በአጀንዳ ልየታ የተሳተፉት የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አዲስ መሃመድ፤ የታሪክ እና ትርክት ጉዳይ የህግ መንግስት፣ የሰንደቅ ዓላማ፣ የአዲስ አበባ ባለቤትንት እና የወሰን ጉዳይ የሃይማኖት፣ የቋንቋ እንዲሁም ከፍርድ ቤት ጀምሮ ተቋማት ነፃ እና ገለልተኛ ሆነው እንዲቋቋሙ በአጀንዳነት ቀርበዋል ብለዋል፡፡
የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ፣ የምርጫ፣ የመንግስት አስተዳደር ስርዓትም ባለው ይቀጥል ወይስ ይሻሻል የሚለው ጉዳይ በሕዝብ ውይይት ውሳኔ እንዲገኝ የአዲስ አበባ አጀንዳ ሆነው መቅረባቸውን ሰምተናል።
ብሄራዊ ጀግና ማነው? ብሄራዊ ጀግናን ጉራጌው፣ ኦሮሞው፣ አማራው ሌላው እንዴት ነው የሚያየው?
ብሄራዊ ምልክት ምንድነው? አንበሳ፣ ፒኮክ፣ ዋልያ፣ ነው ወይስ ሌላ ነው የሚለው እንዲለይ የአዲስ አበባ አጀንዳ ሆኖ መቀረቡን አዲስ መሃመድ ነግረውናል።
አዲስ አበባ ባለቤቱ ማን ይሁን? ወሰኑ እስከየት ይሁን? ቋንቋዋ ምን ይሁን? በፌደሬሽን ምክር ቤት ውክልናዋ ምን ይሁን? የሚሉ ጥያቄዎች በምክክር እንዲፈቱ አጀንዳ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
ትናንት በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው የመጀመሪያ ምዕራፍ ምክክር የሀገሪቱ የምርጫ ሰርዓት በድምፅ ብልጫ ወይስ በሌላ አማራጭ ይወሰን እንዲሁም ከፍርቤት ጀምሮ በከተማዋ ያሉ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በአጀንዳ መቅረባው ተነግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
Comments