ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ወደብ ውጪ ሌሎች አማራጭ ወደቦችን እየተጠቀመች መሆኑን ተነገረ፡፡
ይህ የተባለው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የ9 ወር ሪፖርቱን ለህዝብን እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርብ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት የወጪ እና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ታደርግ የነበረው በጅቡቲ ወደብ በኩል የነበረ ሲሆን አሁን ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር በተደረገ ድርድር አማራጭ ወደቦችን እየተጠቀመች ነው ተብሏል፡፡
የትራንስ ፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚንስትር አለሙ ስሜ የታጁራ፣ በርበራ፣ ሞምባሳ እና ላሙ ወደብን በአማራጭነት መጠቀም በመቻሉ አላግባብ የሚባክን ጌዚ እና የውጪ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ9 ወራት ውስጥ 8.8 ሚልየን አለማቀፍ መንገደኞችን አጓጉዟል፡፡
2.4 ሚልየን የሚሆኑ ደግሞ የሀገር ውስጥ መንገደኞችን ማጓጓዙን ተነግሯል፡፡
አየር መንገዱ በዚህ ወቅት 178 አውሮፕላኖችን ለበረራ እየተጠቀመ ነው፡፡
ሚኒስትሩ አለሙ በሪፖርታቸው እንቀጠቀሱት በተለያዩ አካባቢዎች 25 የሚጠጉ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያዎች እየተገነቡ ሲሆን ግንባታዎቹ የሚከወኑት በክልል መንግስታት እና በግል ባለሀብቶች ነው፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ባለፉት 9 ወራት ከ2 ሚልየን በላይ አሽከርካሪዎች ጥፋት አጥፍተው በመገኘታቸው ተቀጥተዋል ያለ ሲሆን ከዚህም 1 ቢልየን ብር ገቢ አግኝቷል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበዛ ያለው የኤሌክትሪክ መኪና ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑንም ተነግሯል፡፡
ለመኪኖቹ የሀይል መሙያ እንዲሰናዳ ለማድረግም የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ለእቃ ማጓጓዣ የሚያገለግሉ ኮንቲነሮች እጠረት አጋጥሞ ነበር የተባለ ሲሆን የመርከቦች የወደብ ቆይታ ዝቅተኛ ለማድረግ ስራዎች መሰራታቸው ሚኒስትሩ አለሙ በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር እና ትርፍ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን ለመቅጣት እየሰራ ነው ተባለ ሲሆን ህብረተሰቡ ለዚህ ትብብር ሊያደርግ ይገባል ተብሏል፡፡
ባለሀብቶች በሎጅስቲክስ ዘርፍ ገብተው ኢንቨስት ማድረግ አለባቸው የተባለ ሲሆን መንግስት ለዚህ ድጋፍ ያደርጋል መባሉን ሰምተናል፡፡
በረከት አካሉ
Comments