top of page

ግንቦት 28፣2016 - ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያችን ተመለሱ እየተባልን ያለነው በውዴታ ሳይሆን በግዴታ ነው ሲሉ ይሰማል

ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያችን ተመለሱ እየተባልን ያለነው በውዴታ ሳይሆን በግዴታ ነው ሲሉ ይሰማል፡፡


የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ ተፈናቃዮቹ የሚመለሱት በጉልበት አይደለም ብሏል፡፡


እነዚህ ተፈናቃዮች ‘’እዚም በመጠለያ ጣብያ ነው የምንኖረው እዚያም ቤታችን ሳይሆን የምንገባው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ነው’’ ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ ‘’ለፀጥታ ስጋት’’ ዳርጎናል ይላሉ፡፡


የሰላም ሚኒስቴር ተፈናቃዮቹን የመመለሱ ዋና ተግባር የሁለቱ ክልሎች ማለትም የአማራ እና የትግራይ ቢሆንም በግጭት የተፈናቀሉትን የማስመለሱን ስራ ግን በጋራ እንደሚሰሩ ተናግሮ በመጠለያ ያደረግናቸው ለጥበቃ እንዲመቸ ነው ብለዋል፡፡


የሰላሙ ሁኔታ ሲረጋገጥ ወደየቤታቸው እንደሚመልሳቸው አስረድቷል፡፡


ተፈናቃዮች እየተመለሱ ያሉት ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ አካባቢዎች እንደሆነና እነዚህ አንፃራዊ ሰላም የተረጋገጠባቸው ናቸው መባሉን ከሰላም ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡


ማርታ በቀለ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page