በኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች የሚረቡ በጎች ቆዳ፤ በጥራት እና ምቾቱ በገዥዎች ተመራጭ እንደሆነ ይጠቀሳል።
ምቾቱ እና ጥራቱ በጎቹ ያሉበትን አካባቢ ቅዝቃዜ ለመቋቋም በሚያበቅሉት ወፍራም ጸጉር ውጤት እንደሆነ፤የቆዳ ውጤቶችን የሚያመርተው ‘’ኮትኬት ትሬዲንግ’’ የተባለው ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ታደሠ ነግረውናል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማም፤የደጋ በጎች ቆዳ ኢትዮጵያን ከተቀረው አለም ከሚለዩ ምርቶች አንዱ ነው ብለዋል።
ጥራቱ እና ምቾቱ ከፍተኛ፤ ተፈላጊነቱም እንዲህ የበዛ ከሆነው የደጋ በጎች ቆዳ ግን ኢትዮጵያ የሚገባትን ያህል እንዳልተጠቀመች ተነግሯል።
Comments