top of page

ግንቦት 28፣2016 - ሱልጣን ባለ 400 ግራም የክሬም ዱቄት ወተት እና ኑራ ባለ 400 ግራም ሱፐር የዱቄት የወተት እንዳትጠቀሟቸው ተብላቹሀል

  • sheger1021fm
  • Jun 5, 2024
  • 1 min read

ሱልጣን ባለ 400 ግራም የክሬም ዱቄት ወተት እና ኑራ ባለ 400 ግራም ሱፐር የዱቄት የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶችን ያላሟሉ በመሆኑ እንዳትጠቀሟቸው ተብላቹሀል።


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር ባወጣው መረጃ እንዳለው ምርቶቹ በገበያ ላይ በመገኘት የገበያ ኢንስፔክሽን ስራ በማከናወን ከገበያ ከተወሰደው ናሙና ነው የደህንነት ጥራት እንዳለባቸው የተረጋገጠው፡፡

በገበያ ቦታ እና ሱፐር ማርኬት ውስጥ ማንኛውም ነጋዴ ሆነ ግለሰብ ሲሸጥ ከተገኙ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እረምጃዎች እንደሚወሰድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር አስጠንቅቋል፡፡


ሱልጣን ባለ 4 መቶ ግራም የዱቄት ወተት እና ኑራ ሱፐር ባለ 4 መቶ ግራም የዱቄት ወተት ምርት የተደነገገውን የጥራት መስፈርት ሳያሟሉ የተገኙ ምርቶች በመሆናቸው ማንኛውም ሸማች በመግዛት እንዳይጠቀም ሲል ሚንስቴር መ/ቤቱ አሳስቧል።

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page