top of page

ግንቦት 27 2017 - ''ባለባቸው የምግብ እጥረት የተነሳ ህፃናት ለሞት ተጋላጭ የሆኑባቸው የህፃናት ማሳደጊያ መኖራቸውን በክትትሌ ደርሼበታለሁ'' ኢሰመኮ

  • sheger1021fm
  • Jun 4, 2025
  • 1 min read

ባለባቸው የምግብ እጥረት የተነሳ ህፃናት ለሞት ተጋላጭ የሆኑባቸው የህፃናት ማሳደጊያ መኖራቸውን በክትትሌ ደርሼበታለሁ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡


ኮሚሽኑ ይህንኑ በተመለከተ ከዚህ ቀደም የሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች መፈፀም አለመፈፀማቸውን መገምገሙን አስረድቷል፡፡


በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት መካከል በአንዳንዶቹ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቀጠሉባቸው ተቋማት መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተናግሯል፡፡


ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ አዳማ ሐረር ሀዋሳ ሻሸመኔና ወላይታ ከተሞች በሚገኘው 21 የህጻናት ማሳደጊያ ተቋማት ከሰብአዊ መብት ጥበቃ አኳያ ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው ምክር ሃሳቦች ምን ያህሉ ተፈጽሟል የሚለውን እና ግኝቶች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህም የተሻሻሉ ጉዳዮች ቢኖርም አሳሳቢነታቸው የቀጠለውን ለይቶ ምክረ ሃሳቦችን ሰጥቷል፡፡


አሳሳቢነታቸው ከቀጠሉት መካከል የምግብ እጥረት በመኖሩ የህፃናቱ የጤና መብት ተጥሷል ተብሏል፡፡


በምግብ እጥረት ምክንያት ህጻናትን እስከ መሞት የሚያደርሱ ሁኔታዎች ላይ እንደሚገኙና ከስድስት ወር በታች የሆኑ ህፃናት ለዚያ አደጋ ተጋላጭ እንደሆኑ ተመልክቼለሁ ብሏዋል፡፡


ይህ በእንዲህ እንዳለ በእነዚሁ ማሳደግያ ተቋማት ከዚህ ቀደም ክፍተት የታየባቸው ጉዳዮች አሁን ላይ መሻሻል ማሳየታቸውንም ሰምተናል፡፡


መሻሻል ከታየባቸው ጉዳዮች መካከል አካል ጉዳተኛ ህፃናትን ማካተት አንዱ ሲሆን የህፃናቱን መረጃ በአግባቡ ሰንዶ ማስቀመጥ የሚለው ይገኝበታል፡፡

ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Recent Posts

See All
የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡

ጥር 12/2018 የኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ማህበር "ስራቸውን በአግባቡ አልሰሩም፣ ህግን አላከበሩም ፣ ኦዲት ሪፖርት ለዓመታት አላቀረቡም ፣ጠቅላላ ጉባዔም ወቅቱን ጠብቀው ማካሄድ አልቻሉም"በሚል ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበባቸውን የቦርድ አባላት በአዲስ ተካ፡፡ የቀድሞ ቦርድ አባላት ስራቸወን በአግባቡ ባለመ

 
 
 

1 Comment


Vansh Sharma
Vansh Sharma
Jun 07, 2025

You would use the escort service with attractive women of Russian Escorts In Lajpat Nagar if you are going to events alone and you think you need the finest sidekick with a young, attractive woman who will show you are different from other people.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page