top of page

ግንቦት 27፣2016 - ከ 100 ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች ከነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚነት ታግደዋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Jun 4, 2024
  • 1 min read

ከ100 ሺህ በላይ ተሸከርካሪዎች ከነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚነት ታግደዋል ተባለ፡፡


የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አደረግሁት ባለው የማጣራት ኦዲት፤ 1,600 ተሽከርካሪዎች ያለአግባብ በመደጎም ሊወስዱት የነበረ 35.2 ሚሊየን ብር ማዳን ችያለሁ ብሏል፡፡


የነዳጅ ድጎማን አለአግባብ ሲጠቀሚ የነበሩ ከ 103 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከድጎማ ተጠቃሚነታቸው እንደታገዱ መደረጉን ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ ተናግረዋል፡፡


ሚኒስትሩ የተቋማቸው የ9 ወራት የሥራ ክንውን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን የነዳጅ ድጎማ ከታለመለት ዓላማ ውጪ እንዲውል ያደረጉት በህግ እንደሚጠየቁ የታጣው ገንዘብም ለመንግስት እንዲመለስ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


አሁን የድጎማ ሥርዓቱ የሚጠቀሙት የሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች እና የከተማ አውቶብስ ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ባለሶስት እግር ተሽከርካዎች ወይም ባጃጅ ታክሲ አነስተኛ እና መለስተኛ የህዝብ ማመላለሽ ተሸከርካሪዎች ግን ሙሉ ለሙሉ ከነዳጅ ድጎማ ሥርዓቱ እንዲወጡ ተደርጓል ተብሏል፡፡


የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በህገ-ወጥ መንገድ የነዳጅ ድጎማ ሲያገኙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የወሰዱት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል ህገ-ወጥ ስራውን ሲሰሩ የነበሩ የመንግስት አካላትም በህግ እንደሚጠየቁ ተናግሯል፡፡



コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page