top of page

ግንቦት 27፣2016 - በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የአፍሪካ የባዮ ቴክኖሎጂ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል

  • sheger1021fm
  • Jun 5, 2024
  • 1 min read

በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የአፍሪካ የባዮ ቴክኖሎጂ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡


በዚህ ኮንግረስ ላይ ከደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ፣ ኬኒያ፣ ከአሜሪካ እንዲሁም ከተለያየ አለም አቀፍ ተቋማት የተወከሉ ሳይንቲስቶች፣ ምሁራን፣ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡


ኮንግረሱን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ማካሄድ ያስፈለገው፤ በባዮ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በአህጉሪቱ የተለያየ ሀገሮች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ለመመካከር፣ ልምድ ለመለዋወጥ ታስቦ መሆኑንን ሰምተናል፡፡


የአፍሪካ ህብረት፣ የአለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባም የቴክኖሎጂ፣ የሳይንስ፣ የፈጠራ ማዕከል ማድረግም የመጀመሪያው የአፍሪካ ባዮ ቴክኖሎጂ ኮንግረስ አላማዎች መሆናቸውን ተሰምቷል፡፡


ባክቴሪያዎችን እየተጠቀሙ ምግብ እና መጠጦችን መስራት ለዘመናት የኖረ ባህላዊ ባዮቴክኖሎጂ ሲሆን በዘመናዊ የባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ደግሞ በሽታን፣ ድርቅን የሚቋቋሙ ዝርያዎች በማወጣት ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል፡፡


የአንድ እፅዋት ቅንጣት ወስዶ በቲሹ ካልቸር በማባዛት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዘሮችን ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሰራጨታቸው ተሰምቷል፡፡


ቡና፣ ሸንኮራ አገዳ፣ ሙዝ፣ አናናስ፣ ቴምር የመሳሰሉት እዚህ ጋር ይጠቀሳሉ፡፡


በዘመናዊ ባዮ ቴክኖ በሚባለው ደግሞ የተለያዩ ምርምሮች ውጤቶች መገኘታቸው የባዮ እና ኢመርጂግ ቴክኖሎጂ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር ካሳሁን ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡


በድርቅ፣ በአየር ንብረት መለወጥ፣ በሰብል ተባይ የመሳሰሉት ተጨምረው የምግብ ዋስትና ችግሩ ፈተና የበዛበት አፍሪካ የባዮ ቴክኖሎጂ ተጠቅማ ችግሮች ለመቅረፍ እስካሁን ምን ተሰራ፣ ማን ጋር ምን ጥሩ ነገር አለ የሚለውን በስፋት የሚመክር የመጀመሪያው የአፍሪካ ባዮ ቴክኖሎጂ ኮንግረስ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል፡፡


ንጋቱ ሙሉ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page