top of page

ግንቦት 26 2017 - የአላባ አንጋጫ ዋቶ የመንገድ ፕሮጀክትን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የኮንትራት ውሉ እንዲከለስለት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጠየቀ

  • sheger1021fm
  • Jun 3
  • 1 min read

የአላባ አንጋጫ ዋቶ የመንገድ ፕሮጀክትን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አሁን ባለው የዋጋ ግሽበት ተሰልቶ የኮንትራት ውሉ እንዲከለስለት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጠየቀ፡፡


ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ መጠናቀቅ የነበረበት የመንገድ ፕሮጀክቱ አስካሁን አፈፃፀሙ 23 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል፡፡


የመንገድ ፕሮጀክቱ አማካሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ተቋራጩ በአግባቡ እና በእቅድ ባለመስራቱ ፕሮጀክቱ በመጠናቀቅያ እድሜው 77 በመቶው አልተሰራም ብሏል፡፡


መንገድ ፕሮጀክቱ እስካሁን የአስፓልት ንጣፍ 7 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል፡፡


ተቋራጩ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን መንገዱን ለመገንባት ከተዋዋልኩ ወዲህ ነዳጅ በ553 በመቶ ዶላር በ287 በመቶ እንዲሁም ሲሚንቶ 330 በመቶ ጭማሪ ስለታየ ይህን ታሳቢ ያደረገ የዋጋ ክለሳ ይደረግልኝ ብሏል፡፡


የፕሮጀክቱ ባለቤት ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በበኩሉ የዋጋ ክለሳ እንደማያደርግ ተናግሯል፡፡


የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በበኩሉ ሶስቱም ተቋማት ለፕሮጀክቱ መጓተት እርስ በዕርስ መወቃቀሳቸውን ትተው በጋራ ሰርተው ፕሮጀክቱን እንዲስረክቡ አሳስቧል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page