top of page

ግንቦት 26፣2016 - የመንግስት ኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርአት አሁን ላይ ለኢትዮጵያ ዶላርም ማምጣት መጀመሩ ተነገረ

የመንግስት የግዥ ስርአት ግልጽ፣ ወጪና ጊዜ ቆጣቢ እንዲሆን አድርጓል የተባለለት ወረቀት አልባ ወይም ኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርአት አሁን ላይ ለኢትዮጵያ ዶላርም ማምጣት ማምጣት መጀመሩ ተነገረ።


ማላዊ የግዥ ስርአቱን ከኢትዮጵያ መግዛቷ የተነገረ ሲሆን ቶጎ እና ሶማሌላንድ ደግሞ ለመግዛት በሂደት ላይ መሆናቸውን ሠምተናል።


በ2014 በዘጠኝ የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በሙከራ ደረጃ የተጀመረው ወረቀት አልባ ወይም ኤሌክትሮኒክ የግዥ ስርአት፤ አሁን በ169ኙም ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እየተሰራበት እንደሚገኝ ተነግሯል።


አሰራሩ መስሪያ ቤቶች ከግዥ ዕቅዳቸው ጀምሮ ያሉ ተግባራት በሙሉ የሚከውኑበት ነው ተብሏል።


በዚህም በመንግስት ግዥ ዙሪያ ግልጽነት እንዲፈጠር አድርጓል ሲሉ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሣ ተናግረዋል።


አንዱ የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ከአጠቃላይ በጀታቸው ወደ 451 ቢሊየን ብሩን ለግዥ እንደሚያውሉት ማወቃችን ነው ብለዋል።


አሰራሩ የመንግስት የግዥ ስርአት ግልጽነት እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ወጪ እና ጊዜንም እየቆጠበ ስለመሆኑ ተጠቅሷል።



Commentaires


bottom of page