በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት፤ በከፍተኛነቱ ከአፍሪካ በ2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል የሚል ሪፖርት ከወራት በፊት ይፉ መደረጉ ይታወሳል።
በአሁ ሰዓትም የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት 23 በመቶ እንደሆነ የገንዘብ ሚኒስቴር ተናግሯል።
ከሁለት አሃዝ ዝቅ አልል ብሎ፤ በተለይ የወር ደሞዝተኛውን እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ኑሮ ያከበደውን የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ መንግስት ጥብቅ የሆነ የገንዘብ እና ፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን አድርጌያለሁ ማለቱ ይታውሳል።
በዚህም፤ መንግስት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደው ቀጥተኛ ብድር አምና ከነበረው 147 ቢሊዮን ብር ዘንድሮ ወደ 57 ቢሊዮን ብር መውረዱን፣ የባንኮች የማበደር መጠን በ14 በመቶ እንዲገታ መደረጉን መንግስት ይጠቅሳል።
የስንዴ እና የሩዝ ምርት እንዲጨምር መደረጉን፣ የተማሪዎች ምገባ፣ ጎስቋላ የአቅመ ደካማ ቤት እንዲታደሱ ማድረጉን የዋጋ ግሽበቱ ለመቀነስ ከሰራቸው ስራዎች መካከል መሆኑን መንግስት ጨምሮ ያስረዳል።
መንግስት ይቅርብኝ ያለው፤ 17 ቢሊዮን ብር የፍራንኮ ቫሉታ ጉዳይም እዙሁ ጋ ይጠቀሳል።
ግን ግሽበቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ራስ ምታት ሆኖ ቀጥሏል።
ንጋቱ ሙሉ
Comments