top of page

ግንቦት 25 2017 - የሀገሪቱ ህገ መንግስት እንዲሻሻል፤ መንግስት አጀንዳ አድርጎ ለምክክር ኮሚሽን አቀረበ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jun 2
  • 1 min read

የክልሎች አወቃቀር ቋንቋ ላይ ሳይሆን አቀማመጥን መሰረት ያደረገ እንዲሆንም የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ ሌሎች የጸጥታ አካላት አጀንዳ አድርገው አቅርበዋል፡፡


እነዚህ አጀንዳዎች የቀረቡት የሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ከፌደራል ባለድርሻ አካላት እና ከማህበራት ጋር ለሶስት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው  የምክክር እና የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃ ግብር  ላይ ነው፡፡


የመንግስትን ተወካይዎች አጀንዳዎችን በንባብ ያቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደ ፤ የሃሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በሚታዩባቸው ጉዳዮች ላይ አጽዕኖት ሰጥተናል ያሉ ሲሆን በተለይ ስጋት የሆኑ እና ስጋት እየሆኑ ያሉ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ ጉዳዮችን መፍታት አስፈላጊ ስለሆነ አራት አጀንዳዎችን ተስማምተን ቀርጸናል ብለዋል፡፡


በዚህም መሰረት በመንግስት እና በህዝብ መካከል መተማመን የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመገንባት ህገመንግስቱ እንዲሻሻል አጀንዳ አድርገናል፣ ምክንያቱም ሀገረ መንግስቱ  ባለቤት፣ መስራች እና ፈጣሪ ማነው በሚለው ላይ ለመግባባት እንዲሁም የመንግስት እና የምርጫ ስረዓቱ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን መመለስ አሰፈላጊ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡


ሌላው መንግስት ከህገመንግስቱ አኳያ እንደታይ የሚፈልገው አጀንዳ እና መልስ የምንሻበት ጉዳይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስተዳደር እንዴት ይሁን የሚለው እና የአካታችነት ጉዳይ ነው ሲሉ  አቶ ጥላሁን አስረድተዋል፡፡

የቡድን እና የግል መብቶች፣ የመሬት እና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም እና የሰንደቅ አላማ ጉዳይዎችም በምክክር እንዲታዩ እና መፍትሔ እንዲገኝ መንግስት አጀንዳ አድርጎ አቅርቧል፡፡


የጸጥታ ተቋማት መሪዎች በፖለቲካ ሳይሆን በክህሎት እንዲመረጡ፣ ክልሎች በቋንቋ ሳይሆን አወቃቀራቸው በጂኦግራፊ እንዲሆን፣ የፖለቲካ ምህዳሩ አሳታፊ እንዲሆን እና የኑሮ ውድነቱ መፍትሄ እንዲበጅለት የጽጥታ ተቋማት ተወካይዎች አጀንዳ አድርገው አቅርበዋል፡፡


በፌደራል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ አጀንዳዎቹን የለየው ሌላው ቡድን የሚዲያ እና የማህበራዊ አንቂ ቡድን ነው ፡፡


የቡድኑን አጀንዳ በንባብ ያቀረቡት ጋዜጠኛ ብሩክ ከበደ አብላጫ ድምጽ ላይ መሰረት ያደረገው የምርጫ ስረዓት እንዲታይ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲጠበቅ፣ የባህር በር ጉዳይ ህገ መንግስታዊ እንዲሆን እና ሌሎች አጀንዳዎችን ለይተናል ብለዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page