ግንቦት 25 2017 - በጎንደር ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች በከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ
- sheger1021fm
- Jun 2
- 1 min read
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተፈናቅለው በጎንደር ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች በከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ላይ መልስ ለመስጠት አልፈቀደም፡፡
በመጠለያ ጣቢያ መኖር ከጀመሩ ከአራት ዓመት በላይ እንደሆናችውም ነግረውናል፡፡
አሁን ላይ ድጋፍ ካገኙ ሶስት ወር እንደሆናቸውም አስረድተዋል፡፡
ተጠልለው የሚገኙበት መጠለያ ጣቢያ እየፈራረሰባቸው እንደሆነና ጉዳዩን ይመለከተዋል ለሚባለው ብናሳውቅም መልስ ማግኘት አልቻልንም ይላሉ፡፡
በዚህም በእድሜ የገፉ አዛውንት፣ እናቶችና ህፃናት ገንዘብ ለማግኘት ብለውና በልቶ ለማደር በወሲብ ንግድ መሰማራታቸውን ተፈናቃዮቹ ነግረውናል፡፡
ከዚህ ቀደም ድጋፍ የሚያቀርቡላቸው ረጂ ተቋማት መውጣታቸው ችግሩን አባብሶብናል ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários