በአማራና ትግራይ ክልል በይገባኛል ውዝግብ ምክንያት፤ ሙሉ በሙሉ ከውጥረት ነፃ ያልሆነው የዋግኽምራ ዞን በርካታ ተፈናቃዮች ያሉበት ነው፡፡
የውሀ እጥረትን እና ድርቅ ተከትለው የሚመጡ ወረርሽኞች የዋግህምራ ዞንን እየፈተኑት መሆኑንም ሰምተናል፡፡
በአካባቢው ያለው የሰላም እጦት ሲታከልበት ችግሩ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል ተብሏል፡፡
ኩፍኝ፣ እከክ፣ የውሻ ባሽታ እና ሌሎችም ወረርሽኞች በዞኑ እየሰፋ መምጣቱን ሸገር ሰምቷል፡፡
ሸገር ይህንን የሰማው ከዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ነው፡፡
ዞኑ በጤናው ዘርፍ ካለበት ችግር ለመውጣት ጥረት እያደረገ ቢሆንም የሰላም እጦት፣ ግብረሰናይ ድርጅቶች ሲያደርጉት የነበሩት ድጋፍ መቀነስ እና ሌሎችም ችግሮች ፈተና ሆኗል የተባለ ሲሆን በህክምና እጦት ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ህፃናት እና ነፍሰጡር እናቶች አሉ ተብሏል፡፡
ስለዚህም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትም ሆኑ እርዳታ ሰጭ የረድኤት ድርጅቶች ችግሩ ባለበት እንዳይቀጥል ትኩረት ሊሰጡት ይገባል ሲል ዞኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…. https://tinyurl.com/4d8ym2h6
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Kommentarer