ወጋገን ባንክ እና ኤምፔሳ ሳፋሪኮም የዲጂታል ገንዘብ ክፍያ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የወጋገን ባንክ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ጎይቶም ገብረፃድቃን እና የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ዋና ኃላፊው አቶ ፖል ካቫቩ ፈርመውታል ተብሏል፡፡
የተደረገው ስምምነት የወጋገን ባንክ ደንበኞች ለሚያገኙት አገልግሎትም ሆነ ለሚሸምቱት ምርት ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳያስፈልጋቸው የኤምፔሳ ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በመጠቀም ክፍያ መፈፀም ያስችላቸዋል ሲሉ አቶ ጎይቶም ጠቅሰዋል፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቺፍ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ኃላፊ አቶ ፖል ካቫቩ በበኩላቸው ከወጋገን ባንክ ጋር የተደረሰው ስምምነትም የባንኩ ደንበኛ የሆኑ የኤምፔሳ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን የዲጂታል ክፍያ አማራጭ በማስፋት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።
ስምምነቱ መሰረት ለደንበኞች ፈጣን የገንዘብ ዝውውር እንዲሁም ክፍያዎችን በቀላሉ መፈፀም የሚያስችል መሆኑን ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ ተናግሯል።
ከወጋገን ብንክ ጋር አብሮ ለመስራት የተፈራረመው ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በገኘው የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢነት ፍቃድ በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎች ማቅረብ ላይ መሆኑን ተናግሯል።
ከተለያዩ ባንኮች ጋርም ይሰራል፡፡
ወጋገን ባንክ "ወጋገን ሞባይል"ሲል በጠራው መተግበሪያ በአምስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሶማሊኛ እና እንግሊዝኛ ቀልጣፋ የሞባይል ባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentários