top of page

ግንቦት 22 2017 - ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው የጥናት እና ምርምር ውጤቶች መደርደሪያ ላይ ውለው ችግር ሲፈቱ እምብዛም አይታይም፡፡

  • sheger1021fm
  • May 30
  • 1 min read

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው የጥናት እና ምርምር ውጤቶች መደርደሪያ ላይ ውለው ችግር ሲፈቱ እምብዛም አይታይም፡፡


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰሯቸው የጥናት እና ምርምር ውጤቶች ፖሊሲ አውጭዎች እና ለሌሎችም አካላት እንደ ግብዓትነት እየተጠቀሙት መሆኑ እየተሰማ ነው፡፡


በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ቀደም ይሰሩ የነበሩ የምርምር ውጤቶች የማህበረሰቡ ችግር ላይ ትኩረት ያላደረጉ ነበሩ፤ ይህም ቢሆን በተወሰነ መልኩ እየተስተካከለ ነው ተብሏል፡፡

ይህ የተባለው ቅድስት ማርያም ዩኒቨርስቲ 23ተኛውን የአፍሪካ የግል ከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡


ዩኒቨርሲቲውም ከዚህ ቀደም የሚሰሩ ጥናት እና ምርምሮች ችግር ሲፈቱ እና የሚመለከታቸው ሲጠቀሙባቸው ማየት የተለመደ አልነበረም አሁን ግን ችግሩ እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል፡፡


በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ያሉ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቹን አስተምሮ ከማስመረቅ ባለፈ ምን ያህሉ ተማሪ ወደ ስራ ገብቷል፣ ምን ያህሉ የመውጫ ፈተና ውጤት አምጥቷል? እና በሌሎች መስፈርቶች ይመዘናሉ ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጦሽኔ ከዛም ባለፈ የትምህርት ተቋማቱ ምን ያህል የምርምር ውጤቶችን ከውነዋል የሚለውን ሳይሆን ምን ያህሉ ጥናት ችግር ፈች ሆነ የሚለውን መመዘን ጀምረናል ብለዋል፡፡


በዚህም መሰረት በአመቱ መጨረሻ ተቋማቱ የሰሯቸው የምርምር ውጤቶች ምን ያህል ችግር ፈች ሆኑ ብለን የምዘና ሂደት እናከናውናለን ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ይህ አሰራርም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ተጀምሯል ብለዋል፡፡


ባለፉት አምስት አመታትም በኢትዮጵያ የሚታተሙ የምርምር ውጤቶች በእጥፍ ጨምሯል የተባለ ሲሆን አብዛኞቹም የሚሰሩት በመንግስት የትምህርት ተቋማት ነው ተብሏል፡፡

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





1 comentario


Neha Dutt
Neha Dutt
31 may

I’ve had wonderful experiences with Saket Escorts Agency. The girls are charming, attentive, and make you feel at ease instantly. If you want to add some excitement and relaxation to your life, Saket Escort Service is the best choice. Their professionalism and commitment to privacy are truly commendable.

Me gusta
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page