የዘርመል ምህንድስና የተደረገባቸው ሁለት የጥጥ ዝርያዎች፤ በኢትዮጵያ ተባዝተው እንዲመረቱ የሚጠበቀው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ይሁንታ ብቻ ነው ተባለ፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት ልውጥ ህያው የጥጥ ዘር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ፤ 311 ሄከታር ላይ ተዘርቶ የነበረ ሲሆን ከዚያ ወዲህ በዋናነት ዘሩን ለመግዛት የውጭ ምንዛሪ በመጥፋቱ ምርቱ ቆሞ ቆይቷል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ግን BT-GT የተባለ GMO የጥጥ ዘሮች በኢትዮጵያ ተባዝተው ለገበሬው እንዲከፋፈሉ እና እንዲመረቱ የሚያስፈልጉ የሳይንሳዊ ምርምር ስራዎች መጠናቀቃቸውን የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት ተናግሯል፡፡
ምርምሩ የተደረገባቸው የጥጥ ዘሮች ተባይ እና ፀረ አረም ኬሚካልን እንደሚቋቋሙ እና ምርታማነታቸውም እየተዘሩ ካሉት በሄክታር የ32 ኩንታል ብልጫ ያለው መሆንን የግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
BT-GT ህያው ልውጥ ጥጥ ምርምር የተካሄደውም በወረር፣ ገዋኔ፣ ወይጦ ኦሞራቴ እና መተማ መሆኑን በኢንስቲትዩቱ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ ዳይሬክተሩ ደጀኔ ግርማ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ምርምር አድርጎባቸው ውጤታቸውንም በተጨባጭ ተረጋግጧል የተባሉ የጥጥ ዝርያዎችን በተመለከተ የተገኙ ሳይንሳዊ መረጃው ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተሰጥቶ ፍቃድ እየጠበቀ መሆኑ ዶ/ር ደጀኔ የነገሩን ሲሆን ፍቃድ ሲሰጥ ዘሩን የሚያመጣው ድርጅት የሚያባዛው ሀገር ውስጥ ለአምራቾች በሽያጭ የሚቀርበውም በሀገሪቱ ገንዘብ ነው ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት 84 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መሸፈኑንን የግብርና ሚኒስትር መረጃ ያሳያል፡፡
የሀገሪቱ አመታዊ የጥጥ ፍላጎት 50 ሺህ ቶን ሲሆን የሚመረተውም ይህንን ያህል ነው ሲል በሚኒስቴር መ/ቤቱ የጥጥር ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ ነግረውናል፡፡
ነገር ግን የሀገሪቱ የምርት ፍላጎት በቅርብ ጊዜ 100 ሺህ ቶን ስለሚደርስ የፍላጎቱን ያህል ለማምረት፣ የምርት ሂደቱንም ወጪ ለመቀነስ የዘረመል ምህድስና የተደረገበት የጥጥር ዝርያ አስፈላጊያችን ነው ብለዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires