top of page

ግንቦት 21 2017- ''ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በሚነሱ እንካ ሰላምታ ሳትጠመድ ረጅሙን ርቀት የሚያስኬደውን የዲፕሎማሲ መንገድ ትከተላለች'' የውጭ ጉዳይ ሚ/ር

  • sheger1021fm
  • May 29
  • 1 min read

''ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት በሚነሱ እንካ ሰላምታ ሳትጠመድ ረጅሙን ርቀት የሚያስኬደውን የዲፕሎማሲ መንገድ ትከተላለች'' ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ለጋዜጠኞች ዛሬ በሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ነው፡፡


የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሳምንታዊ መግለጫቸው ኢትዮጵያ በየጊዜው በሚነሱ እንካ ሰላምታ ሳትጠመድ ረጅሙን የዲፕሎማሲ መንገድ ትከተላለች ብለዋል፡፡፡


አምባሳደሩ ይህን ያሉት ባለፈው ግንቦት 16 ቀን 34ኛውን የኤርትራ ነፃነት ቀንን በማስመከት የኤርትራ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ላይ ያቀረቡትን ትችት በተመለከተ ጋዜጠኞች በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው ግንኙነት ማብራሪያ በጠየቁበት ወቅት ነው፡፡


አምባሳደሩ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ የውጪ ግንኙነት አንዱ አንኳር ጉዳይ ከጎረቤት አገራት ጋር ተቀራርቦና ተባብሮ መስራት መሆኑን አስታውሰው በዚህም ሰላምና መረጋጋት ማረጋገጥ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡


ከዚህ ቀደም ከጎረቤት ሀገራት ጭምር በመሪዎች ደረጃ የተለያዩ ክሶች፣ ውንጀላዎች እና ዘለፋዎች የመጡበት አጋጣሚ መኖሩን አምባሳደሩ ጠቁመው ኢትዮጵያም ይህን ጉዞ በሰከነ መንገድ ተወጥታዋለች ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ በየጊዜው በሚነሱ እንካ ሰላምታዎች ሳትጠመድ ከጎረቤት አገራት ጋር ሰላም ላይ የተመሰረተውን ረጅም የዲፕሎማሲ ጉዞ መራመዷን የጠቀሱት አምባሳደሩ የሰሞኑን ጉዳይ በዚህ አግባብ መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ የተረጋጋና የሰከነ አካሄድ እንደምትከተልም አምባሳደሩ ጠቁመዋል፡፡


አገሪቱ አሁንም ከጎረቤት አገር ጋር ትብብርን መሰረት ያደረገ ግንኙነቷን እንደምትቀጥል አምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡


በሳምንታዊ መግለጫቸው አምባሳደሩ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አስመልክተው ባደረጉት ንግግርም ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቿን ከምይንማር ማስመለሷን፣ በተመሳሳይ መንገድ ተመልሰው ወደዚያ መንገድ የሚያቀኑ ዜጎች መኖራቸውን አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page