top of page

ግንቦት 21፣2016 - በሀገር አቀፍ በሚካሄደው የምክክር ጉባኤ 3,500 ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ

በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የምክክር ጉባኤ 3,500 ተወካዮች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡

 

ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ሆነው የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮችን የማሰባሰቡ ስራ ዛሬ በአዲስ አበባ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

 

አጀንዳዎቹ በመጨረሻ ለሚደረገው የምክክር ጉባኤ 3,500 ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች እንደሚሳተፉ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ለሸገር ተናግረዋል፡፡

 

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በአዲስ አበባ በአደዋ ሙዚየም የመጀመሪያ ዙር የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የምክክር ምዕራፍ እያካሄደ ይገኛል፡፡

 

ኮሚሽነር  ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) እየተካሄደ ካለው የምክክር ጉባኤ ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ኮሚሽኑ ይጠብቃል ብለዋል፡፡

እነሱም አንጀንዳ የማሰባሰብ፣ በአጀንዳዎቹ ላይ ጥልቅ ውይይት ማካሄድ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የምክክር ጉባኤ አዲስ አበባ ተወክለው የሚሳተፉ ተወካዮችን መምረጥ እንደሆነ ነግረውናል፡፡

 

ተሳታፊዎቹም አንዱ የሌላውን ሀሳብ የማክበር፣ የመደማመጥ እና ሀሳባቸውን በነፃነት የመግለፅ ይጠበቀባቸዋል፡፡

 

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያ ምዕራፍ የአጀንዳ ማሰባሰቢያ ምክክር በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን ለተከታታይ 7 ቀናት የሚካሄድ ነው፡፡

 

በዛሬው መድረክ ከአዲስ አበባ ከ 119 ወረዳዎች የተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

 

ያሬድ እንዳሻው

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Comments


bottom of page