top of page

ግንቦት 20፣2016 - በሙስና የተመዘበረን ሀብት የሚያስመልስ ገለልተኛ ተቋም እንቋቋም የሚጠይቅ የፖሊሲ ረቂቅ እየተሰናዳ ነው ተባለ፡፡

በሙስና የተመዘበረን ሀብት የሚያስመልስ ገለልተኛ ተቋም እንቋቋም የሚጠይቅ የፖሊሲ እረቂቀው እየተሰናዳ ነው ተባለ፡፡


የፖሊሲ ረቂቁ ‘’የስነምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ፖሊሲ’’ የሚሰኝ ነው ተብሏል፡፡


ረቂቅ ፖሊሲው ፀድቆ ወደስራ የሚገባ ከሆነ በፀረ ሙስና ትግል እስካሁን በሀገር ደረጃ ወጥቶ ተግባራዊ የሆነ የመጀመርያው የፀረሙ ሙስና ፖሊሲ ይሆናል ሲል የተናገረው የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ነው፡፡


ረቂቅ ፖሊሲው ምን ፋይዳ አለው ምን የተለየ ነገር አለው ያልናቸው በስነ ምግባርና ጸረሙስና ኮሚሽን የኮሚሽነር ፅህፈት ቤት አማካሪ መስፍን በላይነህ የፖሊሲ ረቂቁ የፀረሙስና ትግሉ በአንድ ተቋም ብቻ እንዳይሆን እና ለሁሉም የመንግስት መስሪያቤቶች እና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ኃላፊነት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡


በዚህም የመንግስት መስሪያቤቶች የሙስና መከላከልን ስራ እንደ መደበኛ የስራ አካላቸው እንዲያደርጉት የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡


የመስርያ ቤቶችን አመታዊ የሙስና መከላከል ስራ የሚከታተልና ድጋፍ የሚያደርግ ምክር ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲቋቋምም ረቂቅ ፖሊሲው ይጠይቃል፡፡

የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን የውሸት ሪፖርትን እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚዘረፍን ሀብት ለመከላከል እንደሚረዳው ተናግሯል፡፡


ረቂቅ ፖሊሲው ሳይደረግ ተደረገ ሳይሰራ ተሰራ እየተባሉ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን ለመከታተልና ለማረጋገጥ ይበጃል ተብሏል፡፡


በሙስና የተመዘበረን ሀብት በፊት የማስመለሱን ስራ ሲሰራ የነበረው የፍትህ ሚንስቴር ነው ያሉት አቶ መስፍን አሁን ግን የተሰናዳው ረቂቅ ለብቻው የተመዘበረን ሀብት የሚያስመልስ ገለልተኛ ተቋም እንዲቋቋም የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡


ያሬድ አንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comments


bottom of page