ግንቦት 2 2017 - በኢትዮጵያ ፅኑ የአዕምሮ ህመም ያለበትን ደረጃ ሊያሳይ የሚችል ሃገራዊ ጥናት እየተከወነ ነው
- sheger1021fm
- May 10
- 1 min read
በኢትዮጵያ ፅኑ የአዕምሮ ህመም ያለበትን ደረጃ ሊያሳይ የሚችል ሃገራዊ ጥናት እየተከወነ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል የሚከወነው ይኸው ጥናት ፅኑ የአእምሮ ህመም ሲከሰት ቤተሰቦች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድነው፤ህመሙ ሲከሰት ሰዎች መፍትሄ ለማግኘት ወደየት መሄድን ይመርጣሉ፤
የሚለውና ሌሎችም ጉዳዮች የትኩረት ማዕከል ሆነው ላለፉት ሁለት ዓመታት በአዲስ አበባ፣በኦሮሚያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች በተመረጡ አካባቢዎች ጥናቱ እየተከወነ መሆኑን ስራውን በበላይነት የሚመሩትና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአእምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል ፕሮፍሰር የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ አለም ነግረውናል፡፡

በአዲስ አበባ በቂርቆስና በልደታ ክፍለ ከተሞች፣ እንዲሁም በኦሮሚያና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጥቂት ወረዳዎች የሚከወን እንደመሆኑ በፅኑ የአእምሮ ህመም ኢትዮጵያ ያለችበትን ያሳያል ወይ ያልቸው አጥኚው፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ጥናቱ ሲጠናቀቅ ነባራዊውን ሃቅ ያሳያል ብለን እንጠብቃለን ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች ይገኙበታልም ብለዋል፡፡
በሂደት ላይ ያለው ጥናት ምን ውጤት ይዞ ይመጣል የሚለው የሚጠበቅ ቢሆንም ስለ አእምሮ ህመም ያለው የማህበረሰቡ ግንዛቤ እተሻሻለ መጥቷል ቢያንስ ማህበረሰቡ ችግሩ በህክምና እልባት ማግነት እንደሚችል መረዳት ጀምሯል የሚሉት ፕሮፌሰሩ ይሁንና አሁንም በአእምሮ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎችን ቤት ቆልፈው የሚያስቀምጡ አሉ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ምንታምር ፀጋው
Yorumlar