ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ 120 ዓመት የሞላቸው ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግኑኝነታቸውን ይበልጥ ለመጥበቅ አንደሚሰሩ ተናገሩ፡፡
120 ዓመቱንዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያሳይ የፎቶ አውደርዕይ በአዲስ አበባ በብሔራዊ ሙዝየም ላይ ተከፍቷል፡፡
ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የመጀመርያው የንግድ ስምምነት ያደረጉት፤ በ1903 በአፄ ሚንሊክ እና በአሜሪካው ተወካይ በሮበርት እስኪነር መካከል እንደነበረም ተወስቷል፡፡
ይህ ስምምነት የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲ እንዲጀምሩና እስካሁን ለ120 አመት እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ በተለይም ከአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት ይፋዊ የሁለትዮሽ የጋራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተለያዩ ሀገራት ጋር እያደረገች አሁን ላይ ደርሳለች፡፡
ለዚህም እንደ ማሳያነት የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት ነው፡፡
ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ 120 ዓመት ያስቆጠሩ ሲሆን ይህንን በማስመለክተም ሰሞኑን የፎቶ አውደርዕይ አዲስ አበባ ብሔራዊ ሙዝየም ላይ ተከፍቷል፡፡
የቱሪዝም ሚንስቴር ሚኒስትር ዴዕታውስለሺ ግርማ እንዳሉት ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚው ዘርፍ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ላለፉት መታት እየሰሩ ነው፡፡
ሀገራቱ እረጅም ዓመታትን በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያሳለፉ ሲሆን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትም እያደሱ መጥተዋል ይላሉ፡፡
![](https://static.wixstatic.com/media/b24dd6_52b8a9d7a70442b389b4226c5fdd7f63~mv2.jpg/v1/fill/w_980,h_746,al_c,q_85,usm_0.66_1.00_0.01,enc_auto/b24dd6_52b8a9d7a70442b389b4226c5fdd7f63~mv2.jpg)
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተጠባባቂ ምክትል አምባሳደር ራያን ብራዲን የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በመተማመን የተመሰረተ ነው ብለዋል፡፡
በትምህርት ጤና ግብርና እና በሌሎ ዘርፎች በጋራ እየሰራን ነው ያሉ ሲሆን በተለይም አሁን ላይ የሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እየጨመረ መጥቷል ለዚህም ማሳያው በአሜሪካ የሚኖሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
![](https://static.wixstatic.com/media/b24dd6_fcc306671d764922b4e5c58ae636881d~mv2.jpg/v1/fill/w_980,h_654,al_c,q_85,usm_0.66_1.00_0.01,enc_auto/b24dd6_fcc306671d764922b4e5c58ae636881d~mv2.jpg)
ለእይታ በተከፈተው የፎቶ ኤግዚቢሽን የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሲመሰረት ጀምሮ እስካሁ ድረስ ያለበት እንቅስቃሴ እንደሚያሳይ ተመልክተናል፡፡
ኤግዚቢሽኑ የተከፈተው በብሄራዊ ሙዝየም ሲሆን እስከ ግንቦት 18 እንደሞቆይ ሰምተናል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments