ኢትዮጵያ "በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት" መሰረት ከ5,800 በላይ የሌሎች ሀገራት ምርቶች ያለ ታሪፍ ወደ ገበያዋ ገብተው እንዲሸጡ ተስማምታለች።
ስጋ እና የስጋ ውጤቶችን ጨምሮ ደግሞ የ453 ምርቶችን የታሪፍ ከለላ ለተወሰነ ጊዜ አላነሳም ብላለች።
በ193 ምርቶች የታሪፍ ጉዳይ ምን ጊዜም አትምጡብኝ ማለቷንም ሠምተናል።
"የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነት" ከስድስት ዓመት በፊት በጎርጎርሳውያኑ 2018 በአርባ አራት አገራት መፈረሙ ይታወሳል።
አሁን ላይ ይህንን ስምምነት ከሃምሳ አምስቱ የአፍሪካ አገራት 54 ፈርመውታል።
ያልፈረመችው ብቸኛ አገር ኤርትራ ናት ።
በአካውንቲንግና ህግ የተመረቁ የሌሎች አገራት ሞያተኞች ጭምር በአገሯ እንዲሰሩ ቃል የሰጠችበት ይህ ስምምነት ምን ያስገኝላታል፤ ምንስ ያሳጣታል?
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments