አዲስ አበባ ላይ ቤት ማግኘት እየከበደም፣ ከአቅም በላይ እየሆነ መምጣቱ ይነገራል፡፡
በተለይም በወርሃዊ ደመወዝ ለሚተዳደር የከተሜው ሰው የአቅሙን ቤት ገዝቶ ለመኖር አሁን አሁን እንደ ጉም የማይጨበጥ ህልም እየሆነ መጥቷል ይባላል፡፡
በየጊዜው አዳዲስ የሪልስቴት ገንቢ ኩባንያዎች እየተበራከቱ ቢመጡም ትኩረታቸው አቅም ያለውን ማህበረሰብ እንጂ ወርሀዊ ደመወዝ ከፍሎ የሚኖረውን ሰራተኛ አይመለከቱም፡፡
ይህንን ክፍተት እሞላለሁ በማለት ከ9 ወር በፊት ስራዉን የጀመረው ኪ ፋይናንስ ሶሉሽን ለመጀመሪያ ጊዜ ባወጣሁት እጣ መሰረት ተመዝግበው ከነበሩ ቆጣቢዎች መካከል 58 የሚሆኑት የቤት ባለቤት እንዲሆኑ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡
የ ተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ አሁንም ትኩረታችን አቅም ኖሮት ቤት መግዛት በማይችለው ማህበረሰብ ነው ብለዋል፡፡
ተቋሙ ከአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሞያዎች ማህበር ስምምነት ያደረገ ሲሆን ስምምነታቸውም የማህበሩ አባላት በ ኪ ሀውሲንግ በኩል እየቆጠቡ ቤት ለማግኘት ያለመ ነው፡፡
Comments