ግንቦት 19 2017 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 9 ወራት 14.5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን ተናገረ፡፡
- sheger1021fm
- May 27
- 1 min read
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 9 ወራት 14.5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን ተናገረ፡፡
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ13 በመቶ እድገት እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡
አየር መንገዱ በዘጠኝ ወር ውስጥ ያገኘው ገቢ 5.6 ቢሊዮን ዶላር መሆኑንን ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የተናገሩት አቶ መስፍን ጣሰው ገቢውም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡

በጊዜ ማዕቀፍ 10 አዳዲስ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድን መቀላቀላቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ኤርባስ A350-1000 መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
በዘጠኝ ወሩ ውስጥ አራት አዳዲስ የበረራ መዳረሻዎችንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መክፈቱ ተጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመጪው ሰኔ ወር ብቻ ሁለት አለም አቀፍ በረራዎችን እንደሚጀምር እንዲሁም ሁለት ኤር ባስ A350-900 አውሮፕላኖችን እንደሚረከብ አቶ መስፍን አስረድተዋል፡፡
በቢሾፍቱ ለሚገነባው ግዙፍ ኤርፖርት የዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑንን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚ የኤርፖርቱን ግንባታ በመጪው ዓመት ህዳር ወር ለመጀመር ታስቧል ብለዋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Creating all of these trained, attractive Escorts in Mahipalpur will provide you with a certain spectrum of pleasure. You would feel revitalized and practically happy as a result of their efforts. Gaining from our settled and established darlings can be facilitated by a stunning event of maximum delight.